አ.አ ዋንጫ / በምድብ “ለ” የመጀመሪያ ጨዋታዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥብ ሲጥል ኢትዮ ኤሌክትሪክ አሸንፏል

የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ(ሲቲ ካፕ) ዛሬ ቀጥሎ የተካሄደ ሲሆን የምድብ “ለ” ክለቦች የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ማድረግ ችለዋል፡፡

ቀድሞ በተካሄደው ጨዋታ የአምናው ሻምፒዮን ኢትዮ ኤሌክትሪክ በበላይ አባይነህ ጎል ተጋባዡን አዳማ ከነማን አንድ ለዜሮ አሸንፎ መውጣት ችሏል፡፡

ቀጥሎ በተካሄደው ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስና መከላከያ የተገናኙ ሲሆን በውጤቱም አሸናፊው ሳይለይ ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡

የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዛሬም የየጨዋታዎቹን ኮከብ ተጫዋቾች መርጦ የሸለመ ሲሆን ከመጀመሪያው ጨዋታ የኤሌክትሪኩን ሱራፌል ዳኛቸው ፣ ከሁለተኛው ጨዋታ ደግሞ የቅዱስ ጊዮርጊሱን አብዱልከሪም ኒኪማን መርጧል፡፡

ውጤቶቹን ተከትሎ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ምድቡን በሶስት ነጥብ መምራት ጀምራል፡፡

ውድድሩ በነገው ዕለትም ቀጥሎ ሲካሄድ የምድብ “ሀ” ሁለተኛ ጨዋታዎች ይደረጋሉ ፤ በዚህ መሰረትም 9:00 ደደቢት ከጅማ አባጅፋር ጋር የሚፋለሙ ሲሆን 11:00 ላይ ኢትዮጵያ ቡናና አዲስ አበባ ከተማ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል፡፡
[ምስል ፦ ከውድድሩ ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ]

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s