ድል / ቲም ካሂል የሶሪያዊያንን ተስፋ አጨለመ

Image result for Australia 2-1 Syria:

በ2018ቱ የሩስያ የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር ላይ ተሳታፊ የነበረቸው እና በውድድሩም አስደናቂ ግስጋሴ ስታደርግ የሰነበተቸው ሶርያ የሩቅ ጉዞ ህልሟ በአውስትራሊያ ተገቷል፡፡

ዛሬ ከሰዓት በተደረገው ፍልሚያም አውስትራሊያ በምንጊዜም ድንቅ ልጇ ቲም ካሂል ጎል ወደ ቀጣዩ ዙር የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ ማለፏን አረጋግጣለች፡፡

ባለፉት ስድስት አመታት በከባድ የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ የምትገኘው የሩቅ ምስራቋ ሀገር ምን አልባት ወደ አለም ዋንጫው የምታልፍ ከሆነ ሰላሟን በመጠኑም ቢሆን ታገኛለች ቢባልም በሲዲኒ በተደረገው ጨዋታ 2-1 በሆነ ውጤት በአውስትራሊያ ተሸንፋ ከአለም ዋንጫው ውጪ ሆኗለች፡፡

አውስትራሊያ በጨዋታው 80 በመቶውን የኳስ ቁጥጥር በማድረግ በሶሪያ ላይ የበላይ የነበረች ሲሆን ከእረፍት በፊት ቲም ካሂል እንዲሁም በጭማሪው 30 ደቂቃ ራሱ ቲም ካሂል ባስቆጠረው ግብ በድምር ውጤት 3-2 ሶሪያን በመርታት የኮንካፍ ዞን 4ኛ የምትወጣውን ሀገር በጥሎ ማለፉ እንደምትገጥም እርግጥ ሆኗል፡፡

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s