ጥቃት / የዛምቢያ ብሔራዊ ቡድን አጥቂ አሌክስ ንጎንጋ ቤተሰብ መኖሪያ ቤት ላይ ጥቃት ደረሰ

ዛምቢያ በናይጄሪያ በተሸነፈችበት ጨዋታ ላይ ግልጽ የግብ እድል ያመከነው አጥቂው አሌክስ ንጎንጋን ለሽንፈቱ ተጠያቂ በማድረግ የተሰበሰቡ የዛምቢያ ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች የተጫዋቹ ቤተሰብ መኖሪያ ቤት ላይ ጥቃት አደረሱ።

ለ 2018 የአለም ዋንጫ ማጣሪያ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የዛምቢያ እና የናይጄሪያ ጨዋታ በባለሜዳዎቹ 1-0 አሸናፊነት ተጠናቋል።

በአሌክስ ኢዎቢ ብቸኛ ጎል አሸናፊ የሆኑት ናይጄሪያዎቹ ከአፍሪካ ወደ ራሺያ ለማቅናት ትኬት የቆረጡ የመጀመሪያ አገር ሆነዋል።

በተቃራኒው ናይጄሪያን ማሸነፍ አልመው ወደ ናይጄሪያ ያቀኑት ዛምቢያዎች ሽንፈትን በማስተናገዳቸው ወደ ራሺያ የማቅናት ህልማቸው መና ቀርቷል።

እንግዳዎቹ በጨዋታው ላይ ጎል ለማስቆጠር እድል ቢያገኙም ሊጠቀሙበት አልቻሉም።በተለይ አጥቂው አሌከስ ንጎንጋ ያመከነው አጋጣሚ ዛምቢያዊያንን በጣም ያስቆጨ ነበር።

በቁጭት ብቻ ያልተመለሱት አንዳንድ የአገሪቷ ደጋፊዎች በመኪና ተሰብስበው የተጫዋቹ ቤተሰብ መኖሪያ ቤት በማቅናት ጥቃት እንደፈጸሙ ታውቋል።

የአካባቢው ፓሊስ በኪትዌ ቺምዊምዊ ከተማ ይኖሩ የነበሩት የተጫዋቹ ቤተሰቦች በተሰበሰቡ ደጋፊዎች ድንጋይ በመወርወር ጥቃት እንደደረሰበት ማረጋገጫ ሰጥተዋል።

የፓሊስ ኦፊሰሯ ቻሪቲ ካታንጋ እንደገለጹት ከሆነ ጥቃቱ የተፈጸመው ደጋፊዎች ለዛምቢያ ሽንፈት አጥቂው አሌክስ ንጎንጋን ተጠያቂ በማድረግ እንደሆነ ጨምረው ገልጸዋል።

ፓሊስም በድርጊቱ የተሳተፉ በቁጥር እስከ አምስት የሚደርሱ ደጋፊዎችን ማሰሩ ታውቋል።

የተጫዋቹ እናትም አንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤቱን በሙሉ ለማጥፋት መዛቱን አስታውሰው ለህይወታቸው እንደሚሰጉ ለአንድ የአገሪቷ ቴሌቭዥን ተናግረዋል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s