30 የባሎን ዶር ዕጩዎች ዝርዝር ይፋ ሆኑ

በፍራንስ ፉትቦል መፅሄት ትናንት (ሰኞ) ይፋ በሆኑት የ2017 የባሎን ዶር ሽልማት 30 ዕጩ ዝርዝሮች ውስጥ ክርስቲያኖ ሮናልዶና ሊዮኔል መሲ ተካተዋል።

የሪያል ማድሪዱ ኮከብ ሮናልዶ እና የባርሴሎና ባላንጣው መሲ ሽልማቱን ለዘጠኝ ጊዜያት ያህል ያነሱ ቢሆንም መሲ በ2015 ሽልማቱን ለአምስተኛ ጊዜ በማግኘት የመጀመሪያው ተጫዋች ነው። 

የፓርቱጋሉ አምበል ሪያል ማድሪድን በተከታታይ ዓመት የሻምፒዮንስ ሊጉን ዋንጫ እና የላ ሊጋውን ዋንጫ ማንሳት እንዲችል በማገዙ የዘንድሮውን ሽልማት በማንሳት ከመሲ ጋር ይስተካከላል ተብሎ ይጠበቃል።

ሮናልዶ በርካታ ተጭዋቾቹን በእጩ ዝርዝር ውስጥ ማካተት ከቻለው የሪያል ማድሪድ ስድስተኛው ተጫዋች መሆንም ችሏል።

የስፔኑ ላ ሊጋ በባሎን ዶሩ ሽልማት ዝርዝር ውስጥ 11 ተጫዋቾችን በማካተት ከአንድ ሶስተኛ በላይ ተጫዋቾችን በማካተት ቀዳሚ ሊግ መሆን ችሏል። ፕሪሚየር ሊጉ በሰባት ተጫዋቾች ይከተላል። ቀጥሎ ያለውን ቦታ ደግሞ አምስት ተጫዋቾችን ማስመረጥ የቻለው የጣሊያኑ ሴሪ ኣ ሲሆን የፈረንሳዩ ሊ 1 እና የጀርመኑ ቡንደስሊጋ እንደቅደም ተከተላቸው አራት እና ሶስት ተጫዋቾችን በማካተት ተከታትለው ተቀምጠዋል።

30 ተጫዋቾች የተካተቱበት ሙሉ የባሎን ዶር ዕጩዎች ዝርዝር ይህን ይመስላል

ኔይማር (ፒኤስጂ)
ሉካ ሞድሪች (ሪያል ማድሪድ)
ፓውሎ ዲባላ (ጁቬንቱስ)
ማርሴሎ (ሪያል ማድሪድ)
ንጎሎ ካንቴ (ቼልሲ)
ልዊስ ስዋሬዝ (ባርሴሎና)
ሰርጂዮ ራሞስ (ሪያል ማድሪድ)
ያን ኦብላክ (አትሌቲኮ ማድሪድ)
ፊሊፔ ኮቲንሆ (ሊቨርፑል)
ድሬስ መርተንስ (ናፖሊ)
ኬቨን ደ ብሩይኔ (ማንችስተር ሲቲ)
ሮበርት ሊቫንዶውስኪ (ባየር ሙኒክ)
ዴቪድ ደ ኽያ (ማንችስተር ዩናይትድ)
ሃሪ ኬን (ቶተንሃም)
ኤዲን ጄኮ (ሮማ)
አንቶኒ ግሪዝማን (አትሌቲኮ ማድሪድ)
ቶኒ ክሩዝ (ሪያል ማድሪድ)
ጂያንሉውጂ ቡፎን (ጁቬንቱስ)
ሳዲዮ ማኔ (ሊቨርፑል)
ራዳሜል ፋልካኦ (ሞናኮ)
ሊዮኔል መሲ (ባርሴሎና)
ፒየር-ኤመሪክ አባምያንግ (ቦሩሲያ ዶርትሙንድ)
ኤዲሰን ካቫኒ (ፒኤስጂ)
ማት ኸመልስ (ባየር ሙኒክ)
ካሪም ቤንዜማ (ሪያል ማድሪድ)
ክርስቲያኖ ሮናልዶ (ሪያል ማድሪድ)
ኤደን ሃዛርድ (ቼልሲ)
ሊዮናርዶ ቦኑቺ (ጁቬንቱስ)
ኢስኮ (ሪያል ማድሪድ)
ኪሊያን ምባፔ (ፒኤስጂ)

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s