ላላፉት ወራት በጉዳት ምክንያት ከሜ ርቀው የነበሩት ዳኒ ሮዝ እና ኤሪክ ላሜላ ወደ ልምምድ መመለሳቸውን ቶትንሀም ሆትስፐርስ ይፋ አድርጓል፡፡
እንደ ክለቡ ዘገባ ከሆነ ተጫዋቾቹ ዋናውን ቡድን ተቀላቅለው ልምምድ የጀመሩ ሲሆን በመጪው ሳምንት መጨረሻም ቶትንሀም ከ በርንማውዝ በሚያደርገው ጨዋታ ወደ ሜዳ ይመለሳሉ፡፡
አርጀንቲናዊው ጥበበኛ ኤሪክ ላሜላ በጉዳት በጉዳት ምክንያት ላላፉት 12 ወራት ወደ ሜዳ ያልገባ ሲሆን ከ2 ጊዜ በላይም ከጉዳቱ ለማገገም ቀዶ ጥገናዎችን አድርጓል፡፡ ተጫዋቹ ለመጨረሻ ጊዜ የሊቨርፑልን ማሊያ አድርጎ የተጫወተው በኢኤፍ ኤል ካፕ በአንፊልድ ሮድ ቶትንሀም በሊቨርፑል በተረታበት ጨዋታ ነበር፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለም የቶትንሀም ሆትስፐርሶች ወሳኝ የመሀል ሜዳ አማካዮች ኬንያዊው ቪክቶር ዋንያማ እና ቤልጄማዊው ሙሳ ደምበሌ በጉዳት ምክንያት ከሜዳ የራቁ ሲሆን የሰሜን ለንደኑ ክለብ ግን ያለ ሁለቱ አማካዮች በሊጉ ከሁለቱ ማንችስተሮች በመቀጠል በ14 ነጥብ እና 9 የግብ ክፍያ 3ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል፡፡
Advertisements