ሩስያ 2018 / 23 ሀገራት ወደ 2018 የአለም ዋንጫ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል

Image result for world cup qualified image'

ከ9 ወራት በኋላ በሩሲያ አስተናጋጅነት የሚካሄደው የአለማችን ታላቁ የእግር ኳስ ውድድር ከሚሳተፉ 32 ሀገራት መካከል ከወዲሁ 23 ሀገራት ማለፋቸውን አረጋግጠውበታል፡፡

ከ1986 የሜክሲኮ የአለም ዋንጫ በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ በታላቁ የእግር ኳስ መድረክ ላይ አሜሪካ የማትሳተፍ ሲሆን በ3 ተከታታይ የአለም ዋንጫዎች ላይ ብዙ ርቀት መጓዝ የቻለችው ኔዘርላንድም ከ2018ቱ የአለም ዋንጫ ውጪ ናት፡፡ የ2 ተከታታይ ጊዜ የኮፓ አሜሪካ አሸናፊዋ ቺሊ በአስገራሚ መልኩ ከዚህ ታላቅ ውድድር ውጪ የሆነች ሌላኛዋ ሀገር ናት፡፡
በአውሮፓ ዞን ሰርቢያ ከ 2006 የአለም ዋንጫ በኋላ ወደ መድረኩ ስትመለስ አይስላንድ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የአለም ዋንጫ ተሳታፊነቷን ትኬት መቁረጥ ችላለች፡፡ ፖርቱጋል ፣ ፈረንሳይ ፣ ፖላንድ ፣ እንግሊዝ ፣ ስፔን ፣ ጀርመን ፣ ቤልጂየም ደግሞ ገና ከወዲሁ በሩሲያው የአለም ዋንጫ ተሳታፊነታቸውን ያወጁ ሌሎቹ የአውሮፓ ሀገራት ናቸው፡፡
ከምድባቸው ጥሩ 2ኛ ሆነው ያጠናቀቁት 8 የአውሮፓ ሀገራት በቀጣይ ወር በደርሶ መልስ ፍልሚያ የአሎም ዋንጫው ተሳታፊነታቸውን ያረጋግጣሉ፡፡ ጣሊያን ፣ ስዊዘርላንድ ፣ ዴንማርክ ፣ ክሮሺያ ፣ ሰዊዲን ፣ ሰሜን አየርላንድ ፣ግሪክ እና ሪፐብሊክ አየርላንድ ደግሞ ለጥሎ ማለፉ የቀረቡ 8 ሀገራት ናቸው፡፡
ከፍተኛ ትንቅንቅ በታየበት የደቡብ አሜሪካ ዞን አርጀንቲና በመጨረሻው ጨዋታ በሊዮኔል ሜሲ ታምራዊ እግሮች ኢኳዶርን በማሸነፍ ስታልፍ ኮሎምቢያ ኡራጋይ እና ብራዚል በዞኑ የበላይ መሆናቸውን ተከትሎ የ2018ቱን የአለም ዋንጫ ትኬት መቁረጥ ችለዋል፡፡
በአስገራሚ ፍልምያ ሶሪያን ከአለም ዋንጫው ውጭ ያደረገችው አውስትራሊያ በጥሎ ማለፉ ከሁንዱራስ ስትጫወት ኒውዚላንድ እና ፔሩም በተመሳሳይ ለታላቁ መድረክ ለመብቃት በወርሀ ህዳር አጋማሽ ወሳኙን ፍልምያ ያደርጋሉ፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s