ሲቲ ካፕ/ ኢትዮጵያ ቡና በሰፊ ጎል ሲያሸንፍ ደደቢትም ድል ቀንቶታል

የምድብ “ሀ” ሁለተኛ ጨዋታ መርሃ ግብሮችን ያስተናገደው የአዲስ አበባ ዋንጫ ዛሬ ቀጥሎ ሲካሄድ ኢትዮጵያ ቡና የምድቡን መሪነት የተረከበበትን ድል አስመዝግቧል፡፡

በመጀመሪያ ጨዋታው በአዲስ አበባ ከነማ ሽንፈትን የተጎነጨው ደደቢት ተጋባዡን ጅማ አባጅፋርን ገጥሞ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ያሸነፈ ሲሆን አንዶህ የብቸኛው ጎል አስቆጣሪ ሆኗል፡፡

ቀጥሎ በተካሄደውና በደመቀ የደጋፊዎች ድባብ ታጅቦ በተካሄደው ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ተጋጣሚው የነበረውን አዲስ አበባ ከተማን 4 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል፡፡

ኢትዮጵያ ቡና ካስቆጠራቸው ጎሎች መካከል ሶስቱን ሳሙኤል ሳኑሚ በማስቆጠር ሃትሪክ ሲሰራ ቀሪዋን ጎል ወንድይፍራው ጌታሁን አስቆጥሯል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ከአሰልጣኝ ድራጋን ፖፓዲች ጋር በጤና ችግር ምክንያት መለያየቱ የተነገረለት ኢትዮጵያ ቡና በአራት ነጥብ የምድቡን መሪነት ተረክቧል፡፡

የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እንደተለመደው የየጨዋታዎቹን ኮከብ ተጫዋቾች የሸለመ ሲሆን የጅማ አባጅፋሩ ሄኖክ አዱኛ ከመጀመሪያው ጨዋታ ኮከብ ሆኖ ሲመረጥ የኢትዮጵያ ቡናው ሳሙኤል ሳኑሚ ከሁለተኛው ጨዋታ ኮከብ መሆን ችሏል፡፡

ውድድሩ በነገው ዕለትም ቀጥሎ የሚካሄድ ሲሆን 9:00 መከላከያ ከአዳማ ከነማ ጋር ሲጫወቱ በ 11:00 ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር የምድብ “ለ” ሁለተኛ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s