አርየን ሮበን ራሱን ከሆላንድ ብሔራዊ ቡድን አገለለ

ፈጣኑ የመስመር ተጫዋች አርየን ሮበን አገሩ ኔዘርላንድ በአሳዛኝ ሁኔታ ከአለም ዋንጫ ውጪ መሆኗን ተከትሎ ከብሔራዊ ቡድን ተጫዋችነት ራሱን ማግለሉን አስታወቀ፡

ሆላንድ የአለም ዋንጫ ማጣሪያ የመጨረሻ ጨዋታውን ዛሬ ምሽት ከስዊድን ጋር አድርጋ 2 0 ብታሸንፍም ወደአለም ዋንጫው የሚወስዳትን ቲኬት ለመቁረጥ 6 ለ 0 እና ከዛ በላይ ማሸነፍ ይጠበቅባት ነበር፡፡

በጨዋታው አገሩን ለሻምፒዮናው ለማብቃት እጅጉን ሲጥር የነበረው ሮበን በግሉ የሆላንድን የድል ጎሎች ቢያስቆጥርም በቂ አልነበረም፡፡ 

ከጨዋታው በኋላ ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታ የነበረው ሮበን “አሁን ሙሉ ትኩረቴን ለክለቤ የምሰጥበት ጊዜ ደርሷል፡፡ ለወጣቶቻችን ችቦውን ለማሰተላለፍ ወስኛለሁ” ብሏል፡፡

ሮበን ከ 2003 ጀምሮ ብርትኳናማውን መለያ ለብሶ አገሩን መወከል የቻለ ሲሆን በሶስት የአለም ዋንጫዎችና በሁለት የአውሮፓ ዋንጫዎች ተሳትፎ ማድረግ ችሏል፡፡ የቀድሞው የቼልሲና የሪያል ማድሪድ የአሁኑ የባየርን ሙኒክ ተጫዋች ሮበን በደቡብ ከፍሪካው የአለም ዋንጫ አገሩን ለፍፃሜ ያበቃ ሲሆን በ2014 የዓለም ዋንጫ አስተናጋጇ ብራዚልን በደረጃ ጨዋታ በማሸነፍ ሶስተኛ ሆኖ በጨረሰው የሉዊ ቫንሃል ስብስብ ወሳኝ ድርሻ እንደነበረው የሚታወስ ነው፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s