ኦዚል ከአርሰናል ጋር ለመቆየት እያደረገው ያለው ድርድር በጥሩ መንገድ ላይ መሆኑን ወኪሉ ተናገረ

ከመድፈኞቹ ጋር በአመቱ መጨረሻ ኮንትራቱ የሚጠናቀቀው ሜሱት ኦዚልን ለማስፈረም ሌሎች የአውሮፓ ቡድኖች በንቃት እየጠበቁ ቢሆኑም ወኪሉ ተጫዋቹ ከአርሰናል ጋር እያደረገው ያለው ድርድር በጥሩ መንገድ እየሄደ መሆኑን አሳውቋል።

የ 28 አመቱ የአጥቂ አማካይ ከሪያል ማድሪድ ወደ አርሰናል ከተዛወረ በኋላ ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን በማቀበል ክህሎቱ ይታወቃል።

ተጫዋቹ ኮንትራቱን ሳያራዝም የውድድር አመቱን መጀመሩ በደጋፊዎች ላይ ስጋት ቢያሳድርም ክለቡ ግን አሁንም በኮንትራት ማራዘሚያ ዙሪያ እየተነጋገረ ይገኛል።

አርሰናል ድርድሩን በአሸናፊነት ማጠናቀቅ ካልቻለ ግን በርካሽም ቢሆን በጥር የዝውውር መስኮት ተጫዋቹን ወደ ገበያ ማውጣቱ እንደማይቀር ይጠበቃል።

ነገርግን ከዚህ ሁሉ በፊት የተጫዋቹ ወኪል ለአርሰናል ደጋፊዎች መልካም ዜናን ነግሯቸዋል።

“በኮንትራት ማራዘሚያ ዙሪያ ከአርሰናል ጋር የሚደረገው ድርድር ቀጥሏል።አሁን መናገር የምችለው ድርድሩ በጥሩ መንገድ እየሄደ መሆኑን ነው።ኦዚል በፕሪምየርሉግ ሌላ 2(3) አመታት መጫወት ይፈልጋል።”ሲል ተናግሯል።

ተጫዋቹ ከአርሰናል የሚለቅ ከሆነ ዩናይትድ እና ኢንተርሚላን ከፈላጊ ክለቦች ውስጥ የሚጠቀሱ ሆነዋል።

አርሰናሎች እንደ ኦዚል ሁሉ የአሌክሲስ ሳንቼዝ የኮንትራት ማራዘሚያ ፊርማ እስካሁን ባለማግኘታቸው ተጫዋቹ በነጻ ክለቡን እንዳይለቅ ተሰግቷል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s