የአይስላንድ የእግር ኳስ ስኬት

22405459_1524105414336371_4016790800040268710_n

ነፃ ሃሳብ – በናታ
ከፈረንሳዩ የአውሮፓ ዋንጫ በኋላ ዳግም ለሩሲያው 2018 እ.ኤ.አ. የዓለም ዋንጫ ከምድቧ በቀዳሚነት ያለፈችውን ጥቂት የህዝብ ቁጥር ያላትን አይስላንድን ስኬት ላስቃኛችሁ ወደድኩ።
የአይስላንድን የእግር ኳስ ውጤት ስንመለከት በጣም አስደናቂ ሆኖ የምናገኘው ከፍተኛ የሆነ ሥራ የተሰራበት እና የተለፋበት ውጤት ነው። በእርግጥ በገንዘብ ረገድ ቢበልጡንም እኛ ጠንክረን ብንሰራ ከነሱ የተሻለ ውጤት ለማግኘት ብዙ እድሎች አሉን። እነዚህን ነጥቦች ብንመለከት እኛ ምን ያህል እምቅ አቅም እንዳለን መታዘብ ይቻላል።
አይስላንድ ሕዝብ ብዛትዋ 335 ሺህ ብቻ ነው። ከዚህ ውስጥ ግማሾቹ ሴቶች ናቸው። ከወንዶችም ውስጥ እድሜያቸው ከ18 እስከ 40 የሆኑት 50 ሺህ አካባቢ ይደርሳሉ። ወንዶችንም ሆነ ሴቶችን እና ታዳጊዎችን አጠቃላይ ደምረን እግር ኳስን የሚጫወቱት ቁጥራቸው ብናሰላው ከ21 ሺህ አይበልጡም። ከዚህ እጅግ በጣም ትንሽ የሆነ ቁጥር ውስጥ እንግሊዝን፣ ሆላንድን፣ ቱርክን የመሳሰሉ ታላላቅ ቡድኖችን የሚያሸንፍ፣ ለአውሮፓ እና ለዓለም ዋንጫ የሚያልፍ ክህሎት ያላቸው ተጫዋቾችን ማፍራት መቻል ተአምር ነው።

በዚህ ላይ አገሪቱ በተፈጥሮ አየር ንብረት አልታደለችም። የአይስላንድ አየር ጠባይ እግር ኳዋስን ለማዘውተር በጣም አስቸጋሪ ነው። ከዜሮ በታች ከሆነው ከሃይለኛው ቅዝቃዜ በተጨማሪ በአንድ ቀን ውስጥ እስከ ሀያ ሠዓታት ድረስ ጨለማ የሚሆንበት ወቅት አለ። እነዚህ ዓይነት ተፈጥሮዋዊ ሁኔታዎች ታዳጊዎች እንደፈለጉ እንዳይጫወቱ የሚያግዱ ቢሆኑም አይስላንዶችን ግን ይህ አላቆማቸውም።

አይስላንድ ከአሜሪካ ጋር ስትነፃፀር

ከአስራ አንድ በላይ አስፈላጊ ነገር ሁሉ በውስጣቸው የተሞላላቸው የቤት ውስጥ የስፖርት ማዘዉተሪያ ማዕከሎችን ገንብተው ችግሩን መፍትሔ ፈጥረውለታል። በተጨማሪም በታዳጊ ማሰልጠኛ ፕሮጀክቶች ላይ በጣም ጠንክረው እየሰሩ ይገኛሉ። ለዚህም ማሳያው ለአራት ተጫዋቾች አንድ የፊፋ ደረጃ ያለው አሰልጣኝ እስከ ማፍራትም ደርሰዋል።

እኛም [ኢትዮጵያውያን] እንደነሱ ጠክረን ከሰራን እንግሊዝን የሚያሸንፍ እና ለዓለም ዋንጫ የሚያልፍ ባይሆንም በአፍሪካ ደረጃ ተፎካካሪ ቡድን መገንባት ይቻላል ብዬ አምናለሁ። ነገሮችን ሁሉ ጨለምተኛ ሆኖ ከማየት ታቅበን በሁሉም መስክ ስኬታማ ስራዎችን ለመስራት ሙያዎችን ሳናበላልጥ ክብር መስጠት ይገባናል። ከተሰራ የማይደረስ ነገር የለምና።

በምኞት ብቻ ሳይሆን የስፖርት ማዘውተሪያዎችን በየአካባቢው በመገንባት፣ ሙያን ለባለሞያ በመስጠት፣ ከቤተሰብ ጀምሮ እስከ ላይ ድረስ እድሜ ማጭበርበርን በጋራ በመከላከል፣ ወጣትና ታዳጊዎችን ከአልባሌ ቦታ በማራቅ ዓላማ ይዘው ተኮትኩተው እንዲያድጉ ማድረግ የመንገዳችን መነሻ ይሆናል። የስፖርት ቡድኖችም የቅርቡን ጊዜያዊ ውጤት ሳይሆን የሩቁን አልመው መንቀሳቀስ ይጠበቅባቸዋል።

ያልተዘራ አይበቅልምና ጠንክረን የአይስላንድን ዓርአያ እንከተል። ቸር እንሰብት!❤️

Advertisements
Posted in Uncategorized

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s