ጡረታ / አርቱሮ ቪዳል ከቺሊ ብሔራዊ ቡድን ጫማውን መስቀሉን አሳወቀ

ቺሊ በብራዚል ተሸንፋ ለ 2018 የአለም ዋንጫ ተሳትፎ ካጣች በኋላ የባየርሙኒኩ አማካይ አርቱሮ ቪዳል ከቺሊ ብሔራዊ ቡድን ጡረታ መውጣቱን አሳወቀ።

አሌክሲስ ሳንቼዝና አርቱሮ ቪዳል አይነት ኮከብ ተጫዋቾችን የያዘችው ቺሊ በብራዚል 3-0 ከተሸነፈች በኋላ በ 2018 በራሺያ ከሚካሄደው የአለም ዋንጫ ውጪ መሆኗል አረጋግጣለች።

በ2010 እና በ 2014 የአለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ላይ ቺሊን ማሸነፍ ችላ የነበረው ብራዚል አሁንም የበላይነቷን በማሳየት በቺሊ የአለም ዋንጫ እጣ ፈንታ ላይ መወሰን ችላለች።

ቺሊያዊያንን ይበልጥ ያስቆጨው ደግሞ የአለም ዋንጫው ተስፋቸው የጨለመው በጎል ልዩነት መሆኑ ነበር።

ከውጤቱ በኋላም የቡድኑ አማካይ አርቱሮ ቪዳል በ 30 አመቱ ከቺሊ ብሄራዊ ቡድን ጡረታ መውጣቱን አሳውቋል።

ቪዳል በትዊተር አካውንቱ በስፓኒሽ በጻፈው ማስታወሻ ላይ “ለሁሉም ነገር ሁላችሁንም አመሰግናለው።በዚህ ሁሉ አመት ላስተማራችሁኝ እንዲሁም በህይወት ውስጥ ሁሉም ነገር በስራ እና በጥረት ሊሳካ እንደሚችል ላሳያችሁኝ ሁሉ አመሰግናለው።” ሲል ተናግሯል።

ቪዳል ለቺሊ የመጀመሪያውን ጨዋታ ማድረግ ከጀመረበት ከ 2007 ጀምሮ 98 ጊዜ ለአገሩ ተሰልፎ በመጫወት 23 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s