አርሰን ቬንገር ስለወቅታዊው የተጫዋቾቻቸው ጉዳት ተናገሩ

አርሰናል በፕሪሚየር ሊጉ ከዋትፎርድ ጋር በሚያደገው ቀጣይ ጨዋታ አሌክሲ ሳንቼዝና ሎረን ኮሸልኒ ስለመሰለፍ አለመሰለፋቸው ዘግይቶም ቢሆን አቋሟቸውን የሚፈትሽ ይሆናል። ሳንቼዝ ቺሊ የዓለም ዋንጫውን ለመቀላቀል ሙከራ አድርጋ ካልተሳካላት ጨዋታ እስካሁን እንደተመለሰ የሚገልፁ መረጃዎች አልወጡም። ኮሸልኒ ደግሞ ተረከዙ ላይ በገጠመው ጉዳት የብሄራዊ ቡድን ጨዋታ አምልጦታል።

ሲኣድ ኮላሲናች የብሄራዊ ቡድን ጨዋታ ላይ የዳሌ ጉዳት የገጥመው መሆኑን ጨምሮ የአርሰናል የብሄራዊ ቡድን ጨዋታ ጉዳት ጠንከር ያለ ሆኗል። በጀርመን ብሄራዊ ቡድን ጨዋታ የታፋ ጉዳት የገጠመው እና ይህ ጉዳቱ ደግሞ ለስድስት ሳምንታት ከሜዳ የሚያርቀው ሽኮድራን ሙስታፊም ጉዳይ የህክምና እርዳታ ከሚያስፈልጋቸው ተጫዋቾች ተርታ አሥመድቦታል። 

ነገር ግን በብሄራዊ ቡድን ጨዋታዎች ወቅት ለእንግሊዝና ለጀርመን ያልተጫወቱት ዳኒ ዌልቤክና መሱት ኦዚል ወደልምምድ ተመልሰዋል። ዌልቤክ በብሽሽት ጉዳት ምክኒያት አርሰናል ከቼልሲ ጋር አቻ ከተለያየበት ጨዋታ አንስቶ ከሜዳ ርቆ ቆይቷል። በሌላ በኩል የጉልበት ጉዳት የኦዚል ዋነኛ ችግር ሆኖ ነበር። ሆኖም ሁለቱም ተጫዋቾች ለቪካሬጅ ሮዱ ጨዋታ ወደሜዳ ተመልሰዋል።

“ሁሉም ተጫዋቾች የሉኝም። ምክኒያቱም የተወሰኑት የሚመለሱት ዛሬ [ሃሙስ] ነው። እንደአሌክሲስ ያሉት የተወሰኑት ደግሞ የሚመለሱት ነገ ነው።” ሲሉ ቬንገር ተናግረው። “ኮላስኒች የዳሌ ጉዳት አለበት። ሙስታፊን ደግሞ ከ4-6 ሳምንታት አጥተነዋል። አሳሳቢ ነገር አለብኝ። ምን እንደማደርግ ነገ ውሳኔ ላይ እደርሳለሁ። ኮሸልኒ ነገ የመጨረሻ [የአቋም] ሙከራ ይደረግለታል። አሁን ግን ዝግጁ አይደለም። በግሉ ልምምድ ሲሰራ ቆይቷል።  ምልክቱ አወንታዊ ነው። ስለዚህ ነገ ሙከራ ይደረግለታል።”

“እሱኑ ራሱኑ አናግረዋለሁ።” ሲሉ የአርሰናሉ አለቃ በብራዚል 3ለ0 ተሸንፎ  የዓለም ዋንጫውን የመቀላቀል ተስፋው ያከተመው የቺሊ ቡድን አባል ስለነበረው ሳንቼዝ ተናግረዋል። አክለውም “ትናንት ከቀትር በኋላ ብራዚል ከቺሊ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ በሙሉ ስመለከት ይብለጥ ሃሳብ ገባኝ። በዚህ ጨዋታ ላይ የትለየ እንክብካቤ ሊደረግለት ይገባ እንደነበር መናገር ይኖርብኛል። በጣም አካላዊ እንቅስቃሴ የበዛበት ጨዋታ ነበር። ነገ ሲመለስ አዕምሯዊ ሁኔታውንም የምፈትሽ ይሆናል።” ሲሉ ፈረንሳዊው አሰልጣኝ ተናግረዋል።

ሳንቼዝ ወይም ኮሸልኒ ወደጨዋታ የማይመለሡ ከሆነ እስቀደሞ የቋንጃ ህመም የገጠመው ፍራንሲስ ኮክሊንን፣ የዳሌ ጉዳት ያለበትን ካሊዩም ቻምበርስን፣ እንዲሁም የረጅም ጊዜ የገዳት ሰለባውን ሳንቲ ካዛሮላን በመቀላቀል የመድፈኞቹን የጉዳት ሰለባ ዝርዝር የሚቀላቀሉ ይሆናል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s