ጎርደን ስትራካን ከስኮትላንድ ብሄራዊ ቡድን ሀላፊነታቸው ተነሱ

4.jpg

የስኮትላንድ ብሄራዊ ቡድን አስልጣኝ የነበሩት እንግሊዛዊው ጎርደን ስትራካን እና ረዳታቸው ከስኮትላንድ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጋር ውይይት ካደረጉ በኋላ በጋራ ስምምነት ከሀላፊነታቸው ተነስተዋል፡፡

የስኮትላንድ እግርኳስ ፌዴሬሽን ዋና ጸሀፊ የሆኑት ስቴዋርት ሬጋን ቦርዱን ወክለው በሰጡት መግለጫ “ቦርዱን በመወከል ጎርደን ስትራካንን ለብሄራዊ ቡድን ለሰጡት አገልግሎት ልናመሰግናቸው እወዳለው፡፡”ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አሰልጣኙ ከ 2013 ጀምሮ የስኮትላንድ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን ለ 2018 የአለም ዋንጫ የማለፍ እድላቸው ከ ስሎቬኒያ ጋር አቻ ከተለያዩ በኋላ ማብቃቱን ተከትሎ ብዙዎቹን ስኮትላንዳዊያን አስከፍቷል፡፡

አሰልጣኙ “ከመጀመሪያው እለት ጀምሮ እንደምለው እኔ ስኮትላንድ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ በመሆኔ በህይወቴ የምኮራበት ነገር ነው፡፡” ሲሉ ቢናገሩም ለአለም ዋንጫ ፕሌይኦፍ ለማለፍ አለመቻላቸው ግን እንደተከፉ አልሸሸጉም፡፡

የእግርኳስ ፌዴሬሽኑም አዲስ አቅጣጫ በመዘርጋት ለዩሮ 2020 ከወዲሁ ለመዘጋጀት አዲስ አሰልጣኝ ፍለጋቸውን እንደሚገምሩ ጨምረው አሳውቀዋል፡፡

 

 

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s