ሲቲ ካፕ / ዛሬ በተካሄዱ ጨዋታዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ ዳግም አቻ የወጣበትን ውጤት አስመዘገበ


የምድብ “ለ” ሁለተኛ ጨዋታ መርሃ ግብሮች ዛሬ የተካሄዱ ሲሆን ሁለቱም ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል፡፡

9:00 በተጀመረው የመጀመሪያ ጨዋታ መከላከያ ከአዳማ ከነማ ጋር የተገናኙ ሲሆን ጨዋታው በ 1 ለ 1 አቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡
በረከት ደስታ አዳማን መሪ ማድረግ የቻለችዋን ጎል ማስቆጠር ቢችልም የየተሻ ግዛው ጎል ጦረኞቹን ነጥብ ተጋርተው እንዲወጡ አስችሏል፡፡

ቀጥሎ የተካሄደው የቅዱስ ጊዮርጊስና የኢትዮ ኤሌክትሪክ ፍልሚያ አብዛኛወን የጨዋታ ጊዜ በኤሌክትሪክ መሪነት የዘለቀ ቢሆንም አዳነ ግርማ በጨዋታው የመጨረሻ ደቂቃዎች ያስቆጠረው ግብ ፈረሰኞቹን ከሽንፈት ታድጓል፡፡ የኢትዮ ኤሌክትሪክን የመሪነት ጎል ከመረብ ያሳረፈው ካሉሻ አልሀሰን ነው፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ 4 ነጥብ መሪነቱን ሲያስጠብቅ ቅዱስ ጊዮርጊስና መከላከያ በእኩል ሁለት ነጥቦች ይከተላሉ፡፡

የሁለቱ ጨዋታ ኮከቦች እንደተለመደው የተመረጡ ሲሆን ከመጀመሪያው ጨዋታ የአዳማ ከነማው ደሳለኝ ደበሽ ፣ ከሁለተኛው ጨዋታ ደግሞ የኤሌክትሪኩ ዲዲዬ ሊብሬ ተመርጧል፡፡

ምስል ፦ ከውድድሩ ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s