ሰር አሌክስና ቦቢ ቻርልተን በኬኒ ዳልግሊሽ ስም የሚሰየመው የስታዲየም መቀመጫ ስፍራ ምርቃት ላይ ሊታደሙ ነው

በአንፊልድ አንድ ክፍለዘመን ያስቆጠረው የተመልካች መቀመጫ ስፍራ ዛሬ አርብ የኬኒ ዳልግሊሽ መቀመጫ የሚል ስያሜ የሚያገኝ ሲሆን፣ በመክፈቻ ስነስርዓቱ ላይ የሚታደሙ እንግዶች ዝርዝርም ይፋ ሆኗል።

ስቴቨን ጄራርድና ጄሚ ካራገር በዳልግሊሽ ጥያቄ መሰረት በስፍራው የሚገኙ ሲሆን፣ አለን ሃንሰን፣ የቀድሞው የክለቡ ስራ አስፈፃሚ ፒተር ሮቢንሰን እንዲሁም በክለቡ የልምምድ ሜዳ ሜልዉድ መዝናኛ ረጅም ጊዜ ያገለገሉት ካሮል እና ካሮላይንም ተገባዥ እንግዶች ናቸው። ከዚህ በተጨማሪ ግን በሁለቱ ክለቦች መካከል የመረረ ተቀናቃኝነት ቢኖርም የአሌክስ ፈርጉሰን እና የቦቢ ቻርልተን በመክፈቻ ስነስርዓለቱ ላይ የሚገኙ ይሆናል።

እስከነገው የሁለቱ ክለቦች የአንፊልድ ጨዋታ ድረስ የዘለቀ በሊቨርፑልና በማንችስተር ዩናይትድ መካከል የነበረውን ባላንጣነት የሚያሳይ ግንኙነት በእንድ ወቅት በዳልግሊሽና በፈርጉሰን መካከል ነበር። 

አሁን ግን ያ ባላንጣነት በእነዚህ የቀድሞ የክለቡ ታሪካዊ ግለሰቦች መካከል የለም። በግለሰቦች መካከል የነበረው የአሰልጣኝነት ጫና በመቅረቱም በየፊናቸው የነበረው ቅራኔ ጊዜ ሽሮታል።

የቀድሞው የኦልትራፎርድ ተቀናቃኞቹ በድግሱ ላይ ለመታደም ፈቃደኞች በመሆናቸው ዳልግሊሽን በእጅጉ አስደስቶታል።

“የፈርጊ ድርጊት ከ1,000 ቃላት በላይ ትርጉም አለው። እሱም ሆነ ቦቢ ይመጣሉ።” ሲል ዳልግሊሽ ገልፃ “በሂልስቦሮው ላይ ያደረጉትን አይነት አሁንም አድርገዋል። ቀደም ብለው ነበር የተገኙት። በሜዳላይም ሆነ ከሜዳ ውጪ በመካከላችን ባላንጣነት ነበር። ነገር ግን እንደዚያ አይነት ነገር ሲመጣ ለማመንታት እንኳ አልሞከሩም። ለእኛ ድጋፍ ለመስጠት ወደዚህ ይመጣሉ። እኛም እንደነሱ እንደምናደርግ ተስፋ አለኝ።” ሲል ዳልግሊሽ ገልፅዋል።

የክሎፑ የሜልዉድ ቢሮ እና የክለቡ ባለቤት የሆነው ፌንዌይ ስፖርትስ ግሩፕ ዳልግሊሽ ለክለቡ ላበረከተው ነገር እንዲሁም የዳልግሊሽ ባለቤት የሆኑት ማሪና ዳልግሊሽ ኤንትሪ ለተሰኘ የከተማው ሆስፒታል ለኬሞቴራፒ ህክምና የሚያግዝ 1.5 ሚ.ፓ ለማሰባሰብ ባደረጉት ስኬት በሊቨርፑል የተመልካች መቀመጫ ስፍራ በስሙ እንዲሰየም የወሰነው ባለፈው የውድድር ዘመን ነበር። 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s