ስንብት/ የአሜሪካ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ብሩስ አሬና በፍቃዳቸው ስራቸውን ለቀዋል

Bruce Arena has stepped down from his role as head coach of the United States

በ2018 የሩሲያ አለም ዋንጫ ማጣሪያ ላይ በትሪንዳድ እና ቶቤጎ 2-1 የተረታው የአሜሪካ ብሄራዊ ቡድን ሽንፈቱን ተከትሎ ከታላቁ የእግርኳስ  መድረክ በመውጣቱ እሳካሁን በርካቶችን እያነጋገረ ይገኛል፡፡

ባሳለፍነው አመት የብሄራዊ ቡድኑን አሰልጣኝነት ከየርገን ክሊንስማን የተረከቡት አሜሪካዊው ብሩስ አሬናም ከብሄራዊ ቡድኑ ውድቀት በኋላ በይፋ ራሳቸውን ከብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝነት ማንሳታቸውን አሳወቀዋል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት አጋማሽ ያልጠተበቀ ሽንፈት በትሪንዳድና ቶቤጎ ያስተናገዱት አሜሪካዊያኑ ከሶስት አስርት አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአለም ዋንጫው ውጪ የሆኑ ሲሆን አሰልጣኙም ለፌዴሬሽኑ ዛሬ ባሳወቁት መሰረት ከብሄራዊ ቡድኑ በገዛ ፍቃዳቸው ስራቸውን መልቀቃቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡

ብሩስ አሬና ከዚህ ቀደም የአሜሪካ ዋናውን ብሄራዊ ቡድን ከ1998 እስከ 2006 ድረስ በዋና አሰልጣኝነት የመሩ ሲሆን 130 ጨዋታዎችን በሁሉም ውድድሮች አድርገው 71 ጨዋታዎችን በድል መወጣት ችለው ነበር ፡፡ በተለይም በ2002 የአሜሪካን ብሄራዊ ቡድን ይዘው እስከ ውድድሩ የሩብ ፍጻሜ ተጉዘዋል፡፡ አሜሪካዊው አንጋፋ በአሜሪካ ሜጀር ሶከር ሊግ የተሳካ ጊዜን ያሳለፉ ሲሆን 5 የሜጀር ሶከር ሊግ ዋንጫዎችን ከ ሎስ አንጀለስ ጋላክሲ እና ዲሲ ዩናይትድ ጋር አሳክተዋል፡፡

የአሜሪካ ብሄራዊ ቡድን ከውድድሩ ባልተጠበቀ መንገድ የማይሳተፍ መሆኑን ተከትሎ በመላው አሜሪካ እና ካናዳ የአለም ዋንጫውን የቴሌቬዥን ስርጭት መብትን የገዛው ፎክስ ስፖርት እስከ 200 ሚሊየን ዶላር ኪሳራ ሊደርስበት እንደሚችልም ከወዲሁ በስፋት እየተነገረ ይገኛል፡፡

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s