አንድሬስ ኤኒየሽታ የሩስያው የአለም ዋንጫ ከስፔን ጋር የመጨረሻ ውድድሩ እንደሆነ አሳውቋል

Andres Iniesta celebrates scoring the winning goal in the 2010 World Cup final for Spain against Netherlands

ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ከባርሴሎና ጋር ኳስ እስኪያቆም ድረስ ኮንትራት የፈረመው ስፔናዊው ኮከብ አንድሬስ ኢንየሽታ በመጪው ክረምት የሚደረገው የአለም ዋንጫ የመጨረሻው ውድድሩ እንደሆነ አሳውቋል፡፡

የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ የስፔን ብሄራዊ ቡድን ምድቡን ምንም ጨዋታ ሳይረታ በበላይነት እንዲያጠናቀቅ ከፍተኛ ሚና የተወጣው የላማስያ አካዳሚ ምሩቁ አንድሬስ ኢኒየሽታ  የሩሲያው  የአለም ዋንጫ የመጨረሻው መሆኑን ለ ሰፖርት ጋዜጣ ተናግሯል፡፡

“በዚህ የአለም ዋንጫ መሳተፌ ለኔ መልካም አጋጣሚ ነው ፡፡ ይህ ውድድር በብሄራዊ ቡድን ደረጃ የማደርገው የመጨረሻዮ ነው ” ሲል ከአለም ዋንጫው በኋላ ከስፔን ብሄራዊ ቡድን ጋር በትልቅ ውድድር ላይ ላይጫወት እንደሚችል ፍንጭ ሰጥትዋል፡፡

ከሀገሩ ስፔን ጋር የ2010 የአለም ዋንጫን እንዲሁም የ2008 እና የ2012 የአውሮፓ ዋንጫን ማንሳት የቻለው አስደናቂው የመሀል ሜዳ ጥበበኛ በ2006 በወርሀ ግንቦት ሲሆን የመጀመሪያ ኢንተርናሽናል ጨዋታውን ማድረግ የቻለው ኮከብ እስካሁን 121 ጨዋታዎች ለስፔን ብሄራዊ ቡድን መጫወት ችሏል፡፡

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s