“ለሪያል ማድሪድ መጫወት እንደምችል አምናለሁ”- ሜምፊስ ዲፓይ

Image result for depay

ጽሁፍ ሀሰን አርጋው

የቀድሞው የፒኤስቪ ኢንድሆቭንና የማንቸስተር ዩናይትድ የመስመር አጥቂ ሜምፊስ ዲፓይ ታላላቅ ተጫዎቾች የእግር ኳስ ህልማቸውን እውን ያደረጉበትን የስፔኑን ሃያል ክለብ መቀላቀል ፍላጎቱ እንደሆነ ገልጽዋል።

በማንችስተር ዩናይትድ ቤት 2 ያልተሳኩ አመታትን ማሳለፍ የቻለው ሆላንዳዊው የመስመር ተጫዋች በአሁኑ ሰዓት በኦሎምፒክ ሊዮን የሚገኝ ሲሆን በፈረንሳይ ሊግ ዋንም መልካም የሚባል ብቃቱን እያሳየ ይገኛል፡፡

“ለሪያል ማድሪድ መጫወት እንደምችል አምናለሁ፣ ይህ አላማየ ነው ፈጣሪ ረድቶኝ እንደሚሳካልኝም  እርግጠኛ ነኝ”  በማለት ህልሙ ሪያል ማድሪድን መቀላቀል እንደሆነ ተናግሯል፡፡  ከደች ሊጉ ቡድን ፒኤስቪ ኮብልሎ ፕሪሚየር ሊጉን የተቀላቀለው ሜምፊስ በማንቸስተር ዩናይትድ ቤት ታሪካዊዋን ሰባት ቁጥር ማሊያ ን ቢያጠልቅም የተወራለትን ያህል ሳይሆን ወደ ፈረንሳዩ ክለብ አምርቷል፡፡

የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን ተሰላፊ ሆኖ ሀገሩን ወደ ሩሲያው የአለም ዋንጫ እንድታልፍ ማድረግ የተሳነው መልከ መልካሙ የ23 አመቱ ሜምፊስ ዲፓይ በዘንድሮው የሊዮን ቆይታው በ 9 ጨዋታዎች 3 ግቦችን አስቆጥሮ 3 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን ማቀበል ችሏል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s