ሊቨርፑል ከ ማንችስተር ዩናይትድ ቅድመ ቅኝት

ጆዞ ሞሪንሆ የሊቨርፑልን ድክመት ለመጠቀም ኃይላቸው፣ የቡድን ቅንጅታቸው እና የመልሶ ማጥቃት አጨዋወት ትጥቃቸው የተሟላ ነው። ይሁን እንጂ ከየርገን ክሎፕ ጋር ካላቸው የቀደም ታሪክ አንፃር በአንፊልድ ለሚኖራቸው ጨዋታ አዲስና የተለየ ስትራቴጂ መጠቀም ይኖርባቸዋል። የማሩዋን ፌላኒ እና ፓውል ፖግባ አለመኖር የማንችስተር ዩናይትድ ትልቁ መጥፎ ዜና ሲሆን፣ የሳዲዮ ማኔ አለመኖር ደግሞ የየርገን ክሎፕ ራስ ምታት ነው። ያለፉት ውጤቶችን ከተመልከትን የሊቨርፑል ብቃት ያን ያህልም መጥፎ የሚባል ባይሆንም በዚህ የውድድር ዘመን ከቀንደኛ ተቀናቃኛቸው ማንችስተር ዩናይትድ ግን በሰባት ነጥቦች ዝቅ ብለው ይገኛሉ። 

የጨዋታ ሰዓት፡ ቅዳሜ  ከቀትር በኋላ 8፡30

የጨዋታ ሜዳ፡ አንፊልድ

ባለፈው የውድድር ዘመን፡ ሊቨርፑል 0-0 ማን.ዩናይትድ

የቀጥታ የቲቪ ስርጭት፡ በእንግሊዝ ስካይ ፕሪሚየር ሊግ፣ በአፍሪካ (ከሰሃራ በታች) ሱፐር ስፖርት 3 እና 11፣ በመካከለኛው ምስራቅ እና በሰሜን አፍሪካ ቢንስፖርት 11 እና ቢንስፖርት 2

የጨዋታው ዳኛ

ግምታዊ አሰላለፍ

ሊቨርፑል

ተቀያሪዎች፡  ካሪዩስ፣ ዋርድ፣ ስተሪጅ፣ ክላቫን፣ ጎሜዝ፣ ሚልነር፣ ሮበርትስን፣ ፍላናጋን፣ ግሩጂች፣ ዉድበርን፣ ሶላንኬ፣ ኦክስሌድ-ቻምበርሌን፣ ማርኮቪች፣ ኢንግስ 

መሰለፋቸው የሚያጠራጥር፡ የሉም

ጉዳት ያለባቸው፡ ላላና (የታፋ)፣ ማኔ (የታፋ)፣ ክላይን (የጀርባ)

በቅጣት ላይ የሚገኙ፡  የሉም

የቀደሙ ውጤቶች፡  ድል፣ድል፣ሽን፣አቻ፣ድል፣አቻ

ካርዶች፡ ቢጫ13 ቀይ1

ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ፡ ሳላህ 4

ማንችስተር ዩናይትድ

ተቀያሪዎች፡ ፔሬራ፣ ሮሜሮ፣ ቱዋንዜቤ፣ ሊንደሎፍ፣ ማታ፣ ሊንጋርድ፣ ማክቶሚናይ፣ ሚቸል፣ ዳርሜን፣ ብሊንድ፣ ሻው፣ ስሞሊንግ 

መሰለፋቸው የሚያጠራጥር፡  የሉም

ጉዳት ያለባቸው፡  ካሪክ (የባት)፣ ፌላይኒ፣ (የጉልበት)፣ ኢብራሂሞቪች፣ ሮኾ (ሁለቱም የጉልበት)፣ ፖግባ (የቋንጃ) 

በቅጣት ላይ የሚገኙ፡  የሉም

ከቀደሙ ውጤቶች፡  ድል፣ድል፣አቻ፣ድል፣ድል፣ድል

ካርድ፡ ቢጫ9 ቀይ0

ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ፡ ሉካኩ 7

የጨዋታው እውነታዎች

በርስበርስ ግንኙነታቸው

 • ሊቨርፑል በመጋቢት 2014 ማንችስተር ዩናይትድን በኦልትራፎርድ 3ለ0 በሆነ ውጤት መርታት ከቻለበት ጨዋታ ወዲህ በስድስት ጨዋታዎች ላይ ማሸነፍ አልቻለም(አቻ2፣ ሽን4)።
 • ዩናይትድ ወደአንፊልድ በመጓዝ ካደረጋቸው ያለፉት የመጨረሻ አምስት የሊግ ጨዋታዎች መካከል ሶስቱን አሸንፏል (አቻ1፣ ድል1)። በሁለቱ ጨዋታዎች ላይ ደግሞ መረቡን አላስደፈረም።

ሊቨርፑል

 • ሊቨርፑል በሁሉም ውድድሮች ላይ በሜዳው ላይ ካደረጋቸው 14 ያለፉት የመጨረሻ ውድድሮች ሽንፈት የገጠመው በአንዱ ብቻ ነው (ድል8፣ አቻ5)። 
 • ይሁን እንጂ ካደረጋቸው ያለፉት ሰባት የሊግና የዋንጫ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው በአንዱ ብቻ ነው።
 • ክሎፕ ከሞሪንሆ ጋር ካደረጓቸው ሰባት የነጥብ ጨዋታዎች ሽንፈት የገጠማቸው በአንዱ ብቻ ነው (ድል3፣ አቻ3)።
 • ኮቲንሆ ባለፉት 12 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ ዘጠኝ ግቦችን እና ሶስት የግብ ዕድሎችን በስሙ አስመዝግቧል።

ማንችስተር ዩናይትድ

 • ዩናይትድ የዛሬውን ጨዋታ አሸናፊ የሚሆን ከሆነ በስምንት ጨዋታዎች 22 ነጥቦችን በመሰብሰብ የፕሪሚየር ሊጉ አዲስ ክብረወሰን ያስመዘግባል። 
 • በ2017 ዓመትም 17 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ መረብን ባለማስደፈር ከየትኛውም ክለብ የላቀ ነው።
 • ዩናይትድ ባደረጓቸው ያለፉት ዘጠኝ ጨዋታዎች በስምንቱ ላይ መረባቸውን አላስደፈረም። 
 • ሉካኩ በክለቡ የመጀመሪያዎቹ ስምንት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ስምንት ግቦችን በመረብ ላይ በማሳረፍ የመጀመሪያው የዩናትድ ተጫዋች ሊሆን ይችላል።
 • ይሁን እንጂ ሉካኩ ከሊቨርፑል ጋር ካደረጋቸው ያለፉት ሰባት ጨዋታዎች ማስቆጠር የቻለው በአንዱ ላይ ብቻ ነው። በአምስቱ ላይ ደግሞ ከነጭራሹም ዒላማውን የጠበቀ ሙከራ ማድረግ አልቻለም።
 • ማርከስ ራሽፎርድ ተሰልፎ በተጫወተባቸው ያለፉት 10 ጨዋታዎች አምስት ግቦችን እና አራት የግብ ዕድሎችን በስሙ ማስመዝገብ ችሏል።
Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s