“ሚሶት ኦዚል በአርሰናል ቤት መቆየት ይፈልጋል” – አርሰን ዌንገር

Mesut Ozil is in talks over a new Arsenal deal and Wenger 'genuinely thinks' the midfielder will stay at the club

በሊቨርፑል በሊጉ ሽንፈት ካስተናገዱ በኋላ በኢሮፓ ሊግ እና በካራባኦ ካፕ እንዲሁም በሊጉ ያደረጓቸውን ጨዋታዎች በሙሉ መርታት የቻሉት መድፈኞቹ አሁን የሰላም አየር መተንፈስ ጀምረዋል፡፡

ሆኖም ግን በክረምት ኮንትራታቸውን የሚያጠናቅቁት የ2ቱ ኮከቦቻቸው ነገር በርካታ ደጋፊዎችን እያሳሰበ ይገኛል፡፡ አርሰን ዌንገርም ይህንን አሰመልክቶ በጋዜጣዊ መግለጫቸው ሚሶት ኦዚል በለንደኑ ክለብ የመቆየት ፍላጎት እንዳለው ተናግረዋል፡፡

በሳምንቱ አጋማሽ በወኪሉ በኩል በመድፈኞቹ ቤት ለተጨማሪ አመታት ለመቆየት ድርድር እንደጀመረ የተነገረለት ጀርመናዊው ጥበበኛ ሚሶት ኦዚል በወርሀ ሰኔ ከአርሰናል ጋር ያለው ኮንትራት የሚያበቃ ሲሆን ከወዲሁም ከከለቡ ጋር ከስምምነት ካልደረሰ እና ውሉን ካላደሰ ከጥር በኋላ  ከፈለገው ክለብ ጋር መደራደር እና በአመቱ መጨረሻ ክለቡን በነጻ የመልቀቅ መብት አለው፡፡

አርሰን ዌንገር እንዳሉት ከሆነ ጀርመናዊው ጥበበኛ በአርሰናል ቤት እንደሚቆይ ከፍተኛ እምነት አላቸው “እርሱ በአሁን ሰዓት ስለቆይታው ምን እንደሚያስብ ባላውቅም በግሌ ግን እርሱ ከእኛ ጋር ለተጨማሪ አመታት አብሮን ይዘልቃል የሚል እምነት አለኝ”  ሲሉ የቀድሞ የሪያል ማድሪድ ኮከብ በመድፈኞቹ ቤት በቀጣይ አመትም ሊቆይ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡

በ2013 ከሪያል ማድሪድ አርሰናልን በወቅቱ ሪከርድ በሆነ ሂሳብ 42.5 ሚሊየን ፓውንድ ፊርማውን ያኖረው ጀርመናዊው ኮከብ በመድፈኞቹ  ቤት የ4 አመት ቆይታው እስካሁን በሊጉ 121 ጨዋታዎችን አድርጎ 41 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s