​አትሌቲኮ ማድሪድ ከ ባርሴሎና የጨዋታ ቅድመ ቅኝት

ባርሴሎና በስፔኑ ፕሪሚየራ ዲቪዚዮን ውድድር ላይ ያደረገው መቶ በመቶ የሆነ ስኬታማ ጉዞ እስካሁን ጠንካራ ፈተና አልገጠመውም። ዛሬ ምሽት ግን በፕሪምየራ ሊጋ ስምንተኛ ጨዋታ ወደ አትሌቲኮ ማድሪድ በማምራት ይፈተናል።

የኤርኔስቶ ቫርቫልዴው ቡድን በዋና ከተማዋ ከመጫወቱ በፊት በውድድር ዘመኑ ያደረጋቸውን ሰባት የላ ሊጋ ጫዋታዎቹን በሙሉ በማሸነፍ ሮዪብላንኮዎቹን በስድስት ነጥቦች እየመራ ይገኛል።

ባሉግራዎቹ አዲሱ የአትሌቲኮ ማድሪድ ስታዲየም የሆነው ዋንዳ ሜትሮፓሊታኖ ባለፈው ወር ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ወዲህ ይህ በሜዳው ላይ የሚያደረጉት የመጀመሪያ ጨዋታቸውም ይሆናል።

የባርሴሎና ጉዳቶች

ኦስማን ዴምቤሌ ባለፈው ወር ከጌታፌ ጋር በተደረገው ጨዋታ በገጠመው የታፋ ጉዳት የቀዶ ህክምና አድርጓል። ፈረንሳያዊ የፊት ተጫዋች ለአራት ወራት ያህልም ከሜዳ ርቆ እንደሚቆይ ይጠበቃል። ይህ ማለት ደግሞ በ2017 በሚደረጉ ጨዋታዎች ላይ በሙሉ የማይሰለፍ ይሆናል።

ራፊንሃና አርዳ ቱራንም በዚህ ጨዋታ ላይ የማይሰለፉ ተጫዋቾች ናቸው።

የባርሴሎና ቅጣቶች

በዚህ የውድድር ዘመን የተወሰኑ ቢጫ ካርዶች (ጄራርድ ፒኬና ጆርዲ አልባ እያንዳንዳቸው በላሊጋው ሶስት ሶስት ቢጫ ካርዶች) ውጪ በቀይ ካርድ ከሜዳ የወጣ የባርሴሎና ተጫዋች የለም።

የባርሴሎና ግምታዊ አሰላለፍ

ኦስማን ዴምቤሌ አሁንም ከሜዳ ርቆ የሚገኝ እንደመሆኑ የባርሴሎናው አሰልጣኝ ኤርነስቶ ቫልቬርዴ በምሽቱ ጨዋታ ከሊዮኔል መሲ እና ልዊስ ስዋሬዝ ጋር ተቀናጅቶ የአጥቂ ክፍሉን የሚመራውን ተጫዋች የግድ መወሰን ይኖርባቸዋል።

ቬርቫልዴ በቀኝ በኩል ሰርጂ ሮቤርቶን፣ ዴኒስ ስዋሬዝን ወይም አሌክስ ቪዳልን የመጠቀም አማራጮች አሏቸው። 

ጄርራድ ዴልፎ ባለፉት ሳምንታት የመሰለፍ ዕድሎችን ሳያገኝ የቆየ ቢሆንም በዚህ ጨዋታ ላይ ግን የመሰለፍ ዕድል ሊኖረው ይችላል።

በሌሎች ቦታዎች ላይ ደግሞ ከካታሎኑ ክለብ ጋር “የዕድሜ ልክ” ኮንትራት በቅርብ ጊዜ የፈረመው አንድሬስ ኢንየስታ ምንም እንኳ የተወሰነ የግጭት ጉዳት ቢኖርበትም ጉዳቱ በአማካኝ ስፍራው ላይ ከመሰለፍ እንደማያግደው ግን ይጠበቃል።

የአትሌቲኮ ዜናዎች

አትሌቲኮ ማድሪድ በላ ሊጋው ጠንካራ የሚባል ጅማሮ የነበረው ሲሆን ከሊጉ መሪ ባርሴሎና ጋር ከመጫወቱ በፊትም በአራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

የዲያጎ ሲሞኒው ቡድን እስካሁን በፕሪሜራ ዲቪዚዮኑ ካደረጋቸው ጨዋታዎች በአዲሱ ስታዲየሙ ዋንዳ ሜትሮፖሊታኖ ላይ ያሸነፋቸውን ሁለት ጨዋታዎች (ከማላጋ እና ሲቪያ ጋር ያደርገቸውን) ጨምሮ አራቱን አሸንፎ በሶስቱ ደግሞ በአቻ ውጤት ተለያይቷል።

ዲያጎ ኮስታ ከቼልሲ ወደአትሌቲኮ የተመለሰ ቢሆንም ክለቡ ባለበት የዝውውር አገዳ ምክኒያት እስከጥር ወር ድረስ ለክለቡ ተሰልፎ ግልጋሎት መስጠት አይችልም። በሌላ በኩል የቀኝ መስመር ተከላካዩ ሲሜ ቭርሳልይኮ ደግሞ በምሽቱ ጨዋታ ላይ የመሰለፉ ነገር አጠራጣሪ ነው።

የጨዋታው አበይት እውነታዎች

አትሌቲኮ ከባርሴሎና ጋር ባደረጋቸው ያለፉት 14 የላ ሊጋ ጨዋታዎች ድል ማድረግ አልቻለም። (ከእነዚህም በስምንቱ ሽንፈት ደርሶበታል።)። ይህ ደግሞ በሁሉም ውድድሮች ላይ ከገጠሟቸው ሁሉ የላቀው ነው።

ሮዪብላንኮዎቹ ባርሴሎናን በላ ሊጋው ማሸነፍ የቻሉት በየካቲት 2010፣ 2ለ1 በሆነ ውጤት ያሸነፉበት ጨዋታ ነው።

ሊዮኔል መሲ አትሌቲኮ ላይ ማስቆጠር ከቻላቸው ግቦች (22)ግቦች በላይ ከፍተኛ ግብ ያስቆጠረው በሲቪያ ላይ ብቻ ነው(23)።

አንቶኒ ግሪዝማን ክለቡ ዋንዳ ሜትሮፖሊታኖ ላይ ባደረጋቸው ሶስቱም ጨዋታዎች ላይ ግብ ማስቆጠር ችሏል (ሁለት በላሊጋው ላይ እና አንድ በሻምፒዮንስ ሊጉ።)

ዲያጎ ሲሞን በአሰልጣኝነት ከባርሴሎና ጋር በተቃራኒ በሁሉም ውድድሮች ላይ ካደረጓቸው 21 ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻሉት ሁለቱን ብቻ ነው። በሰባቱ አቻ ሲለያዩ በ12 ጨዋታዎች ላይ ደግሞ ሽንፈት ደርሶባቸዋል።

የቀጥታ ስርጭት የቴሌቪዥን ሽፋን

በአትሌቲኮና በባርሴሎና መካከል በዋንዳ ሜትሮፓሊታኖ የሚደረገው ጨዋታ ቅደሜ ምሽት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጠጠር 3፡45 ላይ ይደረጋል። ይህን ጨዋታ ደግሞ በዩናይትድ ኪንግደም ስከይ ስፖርትስ ፉትቦል ቻናል፣ ከሰሃራ በታች በአፍሪካ በመልቲ ቾይዙ ሱፐር ስፖርት እንዲሁም ሰሜን አፍሪካና በመካከለኛው ምስራቅ አከባቢዎች በቢንስፖርት በቀጥታ ይተላለፋል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s