“ማንችስተር ዩናይትድ የመጨረሻ ክለቤ አይደለም ”- ጆዜ ሞሪንሆ

Manchester United boss Jose Mourinho says he will not retire at Old Trafford

ከ ቀያዮቹ ሰይጣኖች ጋር ከወዲሁ መልካም የሚባል አመት ያሳለፉት ጆሴ ሞሪንሆ ለእርሳቸው ማንችስተር ዩናይትድ  የመጨረሻ ክለባቸው እንደማይሆን ተናግረዋል፡፡ ፖርቱጋላዊው አለቃ  የሊዊ ቫንሀልን ስንብት ተከትሎ ቲያትር ኦፍ ድሪምስ ከደረሱ በኋላ 3 ዋንጫዎችን ከክለቡ ጋር ከፍ  ማድረግ የቻሉ ሲሆን  በዩናይትድ ቤትም ጡረታ መውጣጥ እንደማይፈልጉ ለፈረንሳዩ ቴሊ ፉት ተናግረዋል፡፡

የ54 አመቱ ጆዜ ሞሪሆ በቆይታቸው “አሁን የዚህ ክለብ አሰልጣኝ ነኝ እርግጠኛ ሆኜ የምናገረው ነገር ቢኖር ግን ማንችስተር ዩናይትድ የአሰልጣኝነት ዘመኔ የመጨረሻው ክለብ አይደለም ፡፡ ሁሌም አዲስ ፈተናዎችን መጋፈጥ እና መመልከት እፈልጋለው ፡፡ ” ሲሉ ከዩናይትድ ውጪ በቀጣይ በሌላ ክለብ አለም እንደሚመለከታቸው ተናግረዋል፡፡

ማንችስተር ዩናይትድ በፕሪሚየር ሊጉ በአንፊልድ ሮድ ከሊቨርፑል ጋር ያለ ግብ 0-0 በተለያየበት ጨዋታ ላይ የተከተሉት የአጨዋወት መንገድ በበርካቶች ተብጠልጥለዋል፡፡ ማንችስተር ዩናይትድ የፊታችን ረቡዕ በኦልድትራፎድ ቤኒፍካን በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊጉ የሚገጥም ሲሆን ከ3 ቀናቶች በኋላ ደግሞ በሊጉ ቅዳሜ አመሻሽ ከአዲስ መጪው ሀደርስፊልድ ታውን ጋር የሚገኛኝ ይሆናል፡፡

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s