ሲቲ ካፕ/ የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የምድብ ለ የፍጻሜ ጨዋታዎች ሰኞ ይደረጋሉ

Image may contain: one or more people, people playing sports and outdoor

12ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ በአዲስ አበባ ስቴዲየም ሞቅ ደመቅ ባለ መልኩ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በርካታ የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ወደ ስቴዲየም እየተመሙበት ባለው ውድድርም በእግር ኳስ ፉክክሩ በላይ የስቴዲየሙ የደጋፊዎች ድባብ ይበልጥ የበርካቶች መነጋገሪያ ሆኗል፡፡

8 ክለቦች እየተሳተፉበት የሚገኘው ውድድር የፊታችን እሁድ ፍጻሜውን የሚያገኝ ሲሆን ከወዲሁም ምድብ ሀ ን በበላይነት ያጠናቀቁት ኢትዮጵያ ቡና እና ጅማ አባ ጅፋር ግማሽ ፍጻሜውን መቀላቀላቸውን አረጋግጠዋል፡፡ ኢትዮጵያ ቡና ምድቡን በ5 ነጥቦች እና በ3 ንጹ ግቦች የበላይ ሆኖ ሲያጠናቅቅ ጅማ አባ ጅፋር ደግሞ ደደቢትን በግብ ክፍያ በመብለጥ በ4 ነጥቦች 2ኛ በመሆን ወደ ግማሽ ፍጻሜው ያለፈ ሌላኛው ክለብ ሆኗል፡፡

ውድድሩ ሰኞ ከሰዓት በአዲስ አበባ ስቴዲየም ሲቀጥል የምድብ ለ 2 ወሳኝ የምድቡ ጨዋታዎች ይደረጉበታል፡፡ በ8 ሰዓት መከላከያ ከኢትዮ አሌክትሪክ ሲገናኙ በ11 ሰዓት ደግሞ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ተጋባዡ አዳማ ከተማ ሌላኛውን  የምድቡን ወሳኝ ጨዋታ ያደርጋሉ፡፡ ይህንን ምድብ  ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ4 ነጥቦች ሲመራ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና መከላከያ ደግሞ በእኩል 2 ነጥቦች 2ኛ እና 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

በሁለቱ ጨዋታዎች ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣አዳማ ከተማ እና መከላከያ ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ ድል ማድረግ ሲጠበቅባቸው ኢትዮ አሌክትሪክ ወደ ግማሽ ፍጻሜው ለማለፍ አቻ በቂው ነው፡፡ የምድቡን 1ኛ ደረጃን የሚይዝ ክለብ ከምድብ ሀ 2ኛ ደረጃን ይዞ ካጠናቀቀው ጅማ አባ ጅፋር ጋር በግማሽ ፍጻሜው ሲፋለም የምድበ ሀ 1ኛ ሆኖ ያጠናቀቀው ኢትዮጵያ ቡና ደግሞ በምድብ ለ ላይ 2ኛ ሆኖ የሚያጠናቅቀውን ክለብ በግማሽ ፍጻሜው የሚያገኝ ይሆናል፡፡

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s