ቻን 2018 / ሞሮኮ የ2018 የአፍሪካ ሀገራት ሻምፕዮንሺፕ(ቻን) እንድታዘጋጅ ተመረጠች

2

በጥር ወር ላይ የሚካሄደው በሀገር ውስጥ የሚጫወቱ ተጫዋቾች ብቻ የሚሳተፉበት የአፍሪካ ሀገራት ሻምፕዮንሺፕ(ቻን)  የሰሜን አፍሪካዊቷ ሞሮኮ እንድታዘጋጅ ተመርጣለች፡፡

ውድድሩን ቀደም ብሎ እንድታዘጋጅ ተመርጣ የነበረው ኬኒያ የነበረች ቢሆንም ዝግጅቷ አጥጋቢ ባለመሆኑ የአዛጋጅነት እድሉ መነሳቱ ይታወሳል፡፡

ካፍ ከኬኒያ የተነሳውን እድል ለማን እንደሚሰጥ እስከአሁን ሳይታወቅ ቆይቷል፡፡አገራችን ኢትዮጵያ ኬኒያን በመተካት ውድድሩን ለማዘጋጀት ፍላጎት እንዳላት ተጠቅሶ የነበረ ቢሆንም ከሳምንት በፊት ከፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት እንደተሰማው ከሆነ ኢትዮጵያ ውድድሩን ለማዘጋጀት ጥያቄ አለማቅረቧ ታውቋል፡፡

ሌሎች ፍላጎት ያሳዩ ኢኳቶሪያል ጊኒ እና ሞሮኮ የነበሩ ሲሆን የካፍ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ትናንት በናይጄሪያ ሌጎስ ባደረገው ስብሰባ ሞሮኮ ውድድሩን እንድታዘጋጅ መወሰኑ ታውቋል፡፡

በፈረንጆቹ ከጥር 12 እስከ የካቲት 4 እንደሚደረግ የሚጠበቀው ውድድር ሞሮኮ በአራት ከተሞች የሚገኙ ስታድየሞችን ማዘጋጀቷ ታውቋል፡፡ከተሞቹም ካዛብላንካ፣አጋዲር፣ማራካች እና ታንጊር ናቸው፡፡

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s