ቻን 2018/ ካፍ ግብጽ በ2018 የቻን ውድድር ላይ እንደምትሳተፍ አሳወቀ

​የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን(ካፍ) የ2018 የአፍሪካ ሀገራት ሻምፕዮንሺፕ(ቻን)አዘጋጅነት ለሞሮኮ መስጠቱን ተከትሎ ግብጽ በውድድሩ ላይ ተሳታፊ እንደምትሆን አሳውቋል።

16 ቡድኖች በሚሳተፉበት ውድድር ካፍ ኬኒያ በበቂ ሁኔታ ዝግጅቷን ባለማድረጓ ሞሮኮ የምስራቅ አፍሪካዊቷን አገር ተክታ ውድድሩን እንድታስተናግድ መርጧል።

የካፍ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ትናንት በናይጄሪያ ያካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ የሞሮኮን አዘጋጅነት ሲያጸድቅ ኬኒያን ተክቶ በውድድሩ ላይ እንድትሳተፍ ደግሞ ግብጽን ተክቷል።

ግብጽ በሞሮኮ ተሸንፋ ከውድድሩ ውጪ ብትሆንም የአዘጋጅነት እድሉ ወደ ሞሮኮ ማምራቱን ተከትሎ ሞሮኮ በቀጥታ በማለፏ አብሯት የተጫወቱት ግብጾች ኬኒያን እንዲተኩ ተደርጓል።

ለግብጾቹም ከ 2009 በኋላ በተመሳሳይ ውድድር ላይ ሲሳተፉ ለመጀመሪያ ጊዜ ይሆናል።

ከጥር 12 እስከ የካቲት 4 ድረስ በሚካሄደው ውድድር የሚሳተፉት አገራት ዝርዝር

ሰሜን አፍሪካ

(2 ያለፉ + አዘጋጅ አገር): ግብጽ፣ሊቢያ፣ሞሮኮ

ምስራቅ አፍሪካ 

(2 ያለፉ):ሱዳን፣ዩጋንዳ

መካከለኛው አፍሪካ

 (3 ያለፉ): ካሜሮን፣ኮንጎ፣ኢኳቶሪያል ጊኒ

ምእራብ አፍሪካ ሀ

(2 ያለፉ):ጊኒ፣ሞሪታኒያ

ምእራብ አፍሪካ ለ

 (3ያለፉ):ቡርኪናፋሶ፣አይቮሪኮስት፣ናይጄሪያ

ደቡብ አፍሪካ

 (3 ያለፉ):አንጎላ፣ናሚቢያ፣ዛምቢያ ናቸው።

Advertisements
Posted in Uncategorized

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s