“አርሰናል የተሸነፈው በፍጹም ቅጣት ምት ውሳኔው ሳይሆን በቁርጠኝነት መፋለም ባለመቻላቸው ነው”- ትሮይ ዲኒ

 

3.jpg

ትናንቱ ምሽት አርሰናሎች ወደ ቪካሬጅ ሮድ አቅንተው በዋትፎርድ 2-1 በተሸነፉበት ጨዋታ ቡድኑ በጨዋታው ተፋልሞ ባለመጫወቱ እንጂ በፍጹም ቅጣት ምት ውሳኔው አለመሆኑ የዋትፎርዱ አጥቂ ትሮይ ዲኒ ተናግሯል፡፡

ተከላካዩ መርትሳከር ከማእዘን የተሸማውን ኳስ በጭንቅላቱ ገጭቶ መድፈኞቹን ቀዳሚ በማድረግ ወደ መልበሻ ቤት እንዲያመሩ ማድረግ ችሎ ነበር፡፡ነገርግን ባለሜዳዎቹ ከእረፍት መልስ ተጭነው በመጫወት ሁለት ጎል አስቆጥረው መውጣት ችሏል፡፡

በተለይ ዋትፎርዶች በመስመር ሲያደርጉት የነበረው እንቅስቃሴ ለአርሰናሎች ከብዶ የታየ ቢሆንም የዳኛው የፍጹም ቅጣት ምት ውሳኔ ግን አግባብ አለመሆኑን ብዙዎቹ ተስማምተውበታል፡፡ነገርግን ፍጹም ቅጣት ምቱን ያስቆጠረው አጥቂው ዲኒ አርሰናሎች የተሸነፉት በፍጹም ቅጣት ምቱ ውሳኔ ሳይሆን በጨዋታው ተፋልመው መጫወት አለመቻላቸው እንደሆነ ተናግሯል፡፡

“ዌንገር በጨዋታው የተሸነፉት በፍጹም ቅጣት ምቱ ውሳኔ በመሆኑ ዳኛውን ተጠያቂ ማድረጋቸው ሰምቻለው፡፡ነገርግን በአንድ የፍጹም ቅጣት ምት ሳይሆን በጨዋታው ሊሸነፉበት የሚችሉበት ሌላ ምክንያት ነበር፡፡ሲል አስተያቱን ሰጥቷል፡፡

ትሮ ዲኒ ቸምሮ አርሰናሎች ለሽንፈታቸው ምክንያት የሆናቸው በጨዋታው ተፋልሞ መጫወት አለመቻላቸው እንደሆነ አሳውቋል፡፡

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s