የአውሮፓ ሊጎች ሳምንታዊ ያልተሰሙ ቁጥራዊ መረጃዎች እና እውነታዎች 

በአለም አቀፍ ደረጃ እጅግ ተወዳጅ የሆኑት 5ቱ ታላላቅ የአውሮፓ ሊጎች በሳምንቱ መጨረሻ ተካሂደዋል ኢትዮአዲስ ስፖርትም በሳምንቱ መጨረሻ በተደረጉት ጨዋታዎች ዙሪያ ትኩስ እና ያልተሰሙ አስደማሚ ቁጥራዊ እውነታዎች እና መረጃዎችን ከታች በሚከተለው መልኩ አጠናቅራለች፡፡ ይህንን ያውቁ ኗሯል የሚል መሰናዶም ይኖረናል።
<!–more–>

⚽ በውድድር ዘመኑ ወጥ የሆነ ብቃት ማሳየት የተሳናቸው መድፈኞቹ የትላንት ምሽቱን የዋትፎርድ ሽንፈት ተከትሎ አሁንም በርከት ያለ ወቀሳን እያስተናገዱ ይገኛሉ፡፡ ከሊጉ ጅማሮ አንስቶ እስካሁን ከሜዳቸው ውጪ ያደረጉትን ጨዋታ በድል ያልተወጡት አርሰናሎች ከ2016 አንስቶ እስካሁን ድረስ በሊጉ 35 የጭንቅላት ኳሶችን በማስቆጠር ግን ቀዳሚ ናቸው፡፡

⚽ ሀገሩን ፖላንድን ወደ 2018 የአለም ዋንጫ የሰደደው የባየር ሙኒኩ አጥቂ ሮበርት ሌዋንዶስኪ 2017 ከገባ ለክለቡ ባየርሙኒክ እና ለሀገሩ ፖላንድ ባደረጋቸው 41 ጨዋታዎች 45 ግቦችን ማስቆጠር ችሏል፡፡

⚽ በርካቶች አሰልቺ ነበር ባሉት ጨዋታ የላንክሻየር ደርቢ ያለግብ ተጠናቋል፡፡ ሁለቱ ክለቦች ባሳለፍነው አመትም በተመሳሳይ በአንፊልድ ሮድ ባደረጉት ጨዋታ ያለ ግብ አቻ የተለያዩ ሲሆን ይህም በሁለቱ ክለቦች የእርስ በእርስ ግንኙነት ታሪክ የመጀመሪያው ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

⚽ ቅዳሜ ምሽት በማራኪው ዋንዳ ሜትሮ ፖሊቲያን ስቴዲም በተደረገው የባርሴሎና እና የአትሌቲኮ ማድሪድ የላሊጋ ጨዋታ 1-1 አቻ ለሆነ ውጤት መጠናቀቁ ይታወሳል፡፡ ይህም ውጤት አሁንም የአትሌቲኮውን አለቃ ዲያጎ ሲሞኔን ከባርሴሎና ጋር ያደረጋቸውን የላሊጋ ጨዋታዎች በሙሉ እንዳያሸንፍ አድርጎታል፡፡ አርጀንቲናዊው ነውጠኛ 12 የሊግ ጨዋታዎችን አትሊቲኮ ማድሪድን እየመራ ከባርሴሎና ጋር ቢያደርግም በ8ቱ ተሸንፎ በ4ቱ አቻ ተለያይቷል፡፡

⚽ ተከታታይ 2 ሽነፈቶችን ያስተናገዱት የአምናው የሊጉ ሻምፒዮኖች ቼልሲዎች አዲሱ የውድድር ዘመን እንደ አምናው ቀላል አልሆነላቸውም ፡፡ በአንቶንዮ ኮንቴ የሚመሩት ሰማያዊዎቹ ከ መስከረም 2016 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜም 2 ተከታታይ ሽንፈት ያስተናገዱበት የውድድር ዘመን ሆኗል፡፡

⚽ በጣሊያን ሴሪያ ደማቅ ጉዞን እያደረገ የሚገኘው የኔፕልሱ ክለብ ናፖሊ በአውሮፓ ካሉ 5 ታላላቅ ሊጎች ውስጥ ያደረጋቸውን የሊግ ጨዋታዎች በሙሉ በማሸነፍ ቀዳሚው ነው፡፡ ዲያጎ አርማነዶ ማራዶና ታሪክ የሰራበት ይህ ክለብ በውድድር ዘመኑ 8 ጨዋታዎች አድርጎ 8ቱንም ድል በማድረግ በሴሪያው አናት ላይ መቀመጥ ችሏል፡፡

⚽ ሕይወት በኢትሀድ አልጋ በአልጋ የሆነችለት ብራዚላዊው ኮከብ ጋብሬል የሱስ በሊጉ መድመቁን ቀጥሏል፡፡ በፔፕ ጋርድዮላ የሚመራው ጦር ፊት አውራሪ የሆነው ታዳጊው ኮከብ በውድድር ዘመኑ በሊጉ ማንችስተር ሲቲዎች ካስቆጠሯቸው 29 ግቦች 10 የእርሱ እጅ አለባቸው፡፡ የ21 አመቱ ኮከብ በሊጉ 8 ግቦችን ሲያስቆጥር 2 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል፡፡

⚽ ባለፉት 7 የሊግ ጨዋታዎች ኳስን እና መረብ አልገናኝ ብሏቸው በርካታ አስከፊ የሚባሉ ሪከርዶችን የሰባበሩት ክርስታል ፓላሶች የአምናውን የሊጉ ሻምፒዮን ቼልሲን በኋይትሮንስ ድል ማድረግ ማድረግ ችለዋል፡፡ በሊጉ ግብ ማስቆጠር ሳይችሉ 731 ደቂቃዎች የቆዩት ፓላሶች ከጎል ድርቃቸው ተላቀዋል፡፡

⚽ ከሪያል ማድሪዶች ጋር መልካም የሚባል የውድድር ዘመንን እያሳለፈ የሚገኘው ፈረንሳዊው አለቃ ዚነዲን ዚዳን በሎስ ብላንኮዎቹ ቤት 100ኛ ጨዋታውን ማድረግ ችሏል፡፡ 2 የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ እና 1 የስፔን ላሊጋን ማሸነፍ የቻለው ውጤታማው አሰልጣኝ ከ100 ጨዋታዎች ውስጥ 75ቱን ሲያሸንፍ በ17ቱ አቻ ወጥቶ በ8ቱ ብቻ ሽንፈት ደርሶበታል፡፡ 273 ግቦችን ሲያስቆጥር 101 ግቦች ደግሞ ተቆጥሮበታል፡፡

⚽ በአሁኑ ሰዓት አለም ላይ ካሉ ድንቅ ግብ ጠባቂዎች መካካል በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው የማንችስተር ዩናይትዱ ስፔናዊ የግብ ዘብ ዴቪድ ደጊያ በፕሪሚየር ሊጉ እጅግ ለግብ የቀረቡ ኳሶችን በማምከን በቀዳሚነት ተቀምጧል፡፡ ስፔናዊው እስካሁን 5 ግብ ሊሆኑ ያለቀላቸውን ኳሶች ማዳን ችሏል፡፡
ይህንን ያውቁ ኗሯል ?

❶ ባሳለፍነው አመት ጫማውን መስቀሉን በይፋ ያወጀው ጀርመናዊው ኢንተርናሽናል ፍሊፕ ላሃም በእግር ኳስ በቆየባቸው ላላፉት 20 አመታት 1ድም ቀይ ካርድ አልተመለከተም፡፡

❷ የቼልሲው ጥበበኛ ኤደን ሀዛርድ ወላጅ እናት እና አባት ኳስ ተጫዋቾች ነበሩ፡፡ እናት ካራይን እንዲሁም አባት ቴሪ ኳስን ስራዮ ብለው ይጫወቱ የነበሩ ቤልጄማዊያን ሲሆኑ የእርሳቸውን ፈለግ በመከትልም ሁለቱ ወንድ ልጆቻቸው ስመ ጥር እግር ኳሰኞች መሆን ችለዋል፡፡

❸ ወርቃማ የስኬት አመታትን በተጫወተባቸው ክለቦች ማሳለፍ የቻለው ስዊዲናዊው ጥበበኛ ዝላታን ኢብራሂሞቪች 5 ቋነቋዎችን አቀላጥፎ መናገር እና ማዳመጥ ይችላል፡፡ የማንችስተር ዩናይትዱ ድንቅ የፊት መስመር ተሰላፊ ስዊዲሽ ፣ቦስኒያን ፣ እንግሊዝኛ ፣ ስፓኒሽ እና ጣሊያንኛ ደግሞ መግባባት የሚችልባቸው ቋንቋዎች ናቸው፡፡

❹ 2ቱ የአለማችን ምርጥ እግር ኳሰኞች ሊዮኔል ሜሲ እና ክርስትያኖ ሮናልዶ በ869 ቀናት የሚበላልጡ ሲሆን የ2ቱ ልጆችም ልክ አንደ እነርሱ ሁሉ የ869 ቀናት ልዩነት አለው፡፡

❺ የአለም ዋንጫ የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪው ሚሮስላቭ ክሎሳ እግር ኳስ ተጫዋች ከመሆኑ ቀደም ብሎ በኮንስትራክሽን ድርጅት ውስጥ በግንበኝነት ይሰራ ነበር፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s