ድል/ ታደለች በቀለ በአምስተርዳም ማራቶን አሸናፊ ሆናለች

https://thumbs.dreamstime.com/z/tadelech-bekele-prague-marathon-ethiopia-volkswagen-held-53676937.jpg

በሆላንድ አምስተርዳም በተካሄደ የ42 ኪሜ የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ታደለች በቀለ አሸናፊ ሆናለች፡፡

አትሌቷ በውድድሩ  አሸናፊነቷ በተጨማሪ የመድረኩን የግሏን ሪከርድ የሰበረች ሲሆን ከውድድሩ መጠናቀቅ በኋላም  ማራቶኑ ሊጠናቀቅ 5 ኪሎ ሜትር ሲቀረው የሆድ ህመም ገጥሟት እንደነበር ገልፃለች፡፡

ታደለች በቀለ 2:21:53 ውድድሩን ለመፈጸም የፈጀባት ሰዓት ሲሆን ሰዓቱም በግሏ እስካሁን ያስመዘገበችው ምርጡ ሆኖ ተመዝግቦላታል፡፡ በውድድሩ ላይ ህመም ገጥሟት የነበረችው ታደለች ከ ድሉ በኋላ ለጋዜጠኞች የማራቶኑ አሸናፊ በመሆኗ ደስታዋን ገልጻለች፡፡ በዚህ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አዝመራ አብርሀ በ3ኛነት ውድድሩን ያጠናቀቀች ሲሆን የገባችበት ሰዓትም 2:25:23  ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

በወንዶች በተደረገው ውድድር ኬንያው ላውረንስ ችሪኖ አሸናፊ የሆነ ሲሆን የአምሰተርዳም ማራቶን ሪከርድ የሆነ 2.05.09 ሰዓት በመግባት የውድድሩን ክብረ ወሰን የግሉ ማድረግ ችሏል፡፡ በዚህ ውድድር ኢትዮጵያዊው ሙሌ ዋሲሁን 4ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀ ሲሆን የገበባት ሰዓት ደግሞ 2:05:39 ነው፡፡

በአለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን IAAF  የወርቅ ደረጃ የተሰጠው ይህ ውድድር 4.643 ተሳታፊዎች የተካፈለቡት ሲሆን ፡፡ ከ127 ሀገራት የተወጣጡ ተካፋዮችም በማራቶኑ ላይ ተሳታፊ እንደነበሩ ተገልጧል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s