ጁቬንቱስ በሊጉ ከ42 ጨዋታዎች በኋላ በሜዳው ሽንፈት ገጠመው

ኢሞቢሌ ሁለት ግቦችን ማስቆጠር በቻለበትና ፓውሎ ዲባላ የፍፁም ቅጣት ምት በሳተበት ጨዋታ ላዚዮ ጁቬንቱስን ከ42 የሊግ ጨዋታዎች በኋላ በገዛ ሜዳው 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ጁቬንቱስ በአሊያንዝ ስታዲየም የነበረው የከዚህ ቀደም የበላይነቶች በሴሪ ኣው ለተከታታይ ስድስት ጊዜያት ሻምፒዮን እንዲሆን ቢያስችሉትም፣ የዚህን ጨዋታ ውጤት ተከትሎ ግን በስኩዴቶው ላይ የነበረው የበላይነት ዘንድሮም በተለመደው መልኩ እንዳይቀጥል ቀላል የማይባል ተቀናቃኘት ሳይገጥመው እንዳልቀረ አመላክቷል።

ባለሜዳዎቹ ከላዚዮ ጋር ያደረጓቸውን ያለፉት ስድስት የሊግ ጨዋታዎችን በሙሉ ምንም ዓይነት ግብ ሳይቆጠርባቸው ማሸነፍ ችለው የነበረ ቢሆንም፣ በዚህ ጨዋታ ግን የከዚህ ቀደም ውጤቶችን መድገም ሳይችሉ ቀርተዋል።

የማሲሚላኖ አሌግሪው ቡድን አይሎ በተጫወተበት የማጀመሪያ አጋማሽ ዳግላስ ኮስታ በጁቬንቱስ የመጀመሪያ ግቡን ማስቆጠር ችሏል።

ይሁን እንጂ የቀድሞ የጁቬ ወጣት ተጫዋች ኢሞቢሌ በ14 ዓመት ጊዜ ውስጥ ላዚዮ ለመጀመሪያ ጊዜ ጁቬንቱስን ማሸነፍ የቻለባቸውን ሁለት ግቦች ማስቆጠር ችሎ እንግዳውን ቡድን አሸናፊ ማድረግ ችሏል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s