ጠቅላላ ጉባኤ/ የኢትዮጵያ ቼስ ፌዴሬሽን 15 ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን አካሄደ

22406298_596000633903508_8975583831811501982_n

የኢትዮጵያ ቼስ ፌዴሬሽን በ2009  15 ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን በትላንትናው እለት በጁፒተር ሆቴል አካሄደ፡፡ የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት እንጅነር ፀደቀ ይሁነ በተገኙበት በተደረገው በዚህ ጠቅላለ ጉባኤ ላይ የ2009 የፌዴሬሽኑ ስራዎች ላይ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

ፕሬዝዳንት እንጅነር ፀደቀ ይሁነ በእለቱም የቼዝ ስፖርት በኢትዮጵያ በመልካም ደረጃ ላይ እንደሚገኝ እና ፌዴሬሽኑ እና ባለድርሻ አካላት የጀመሩትን ስራዎች ተጠናክሮ መቀል እንዳለበት አሳስበዋል፡፡  ፕሬዝደንቱ ጨምረው እንደተናገሩትም በቼዝ ስፖርት ዙሪያ በክልሎች በኩል የሚሰሩ ስራዎች ከፍተኛ ድርሻ ስላለቸው ከወትሮ በላይ በጋራ ከፌዴሬሽኑ ጋር ክልሎች በጋራ መስራት አለባቸው ብለዋ፡፡
በዕለቱ የተለያዩ አጀንዳዎች በጉባዔው ላይ ቀርበው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን ለመጀመርያ ጊዜ የ2ኛ ደረጀ የቼስ የዳኝነት ስልጠና ፣ አገር አቀፍ የቼዝ ሻምፒዮና ውድድር፣ የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ የተደረገ ውድድር ፣ ለዩኒቨርስቲ መምህራን የመጀመሪያ  ደረጀ የአሰልጣኝነት ስልጠና እንዲሁም የ2017 የአፍሪካ ዞን 14. 2 በሀገራችን ጂማ ከተማ ላይ የተደረገውን ውድድር በተሳካ ሁኔታ በመስተናገድ በኩል የነበሩትን ስራዎች ጉባኤው  ተወያይቶባቸዋል፡፡

በተጨማሪም የፌዴሬሽኑ የ2010 ዓ.ም የልማት ዕቅድ ፣ የፋይናንስ መመሪያ ፣ የኢትዮጵያ ቼስ ፌዴሬሽን አስልጣኞች፣  የዳኞች እና የስፖርተኞች የምልመላ እና የስልጠና መመሪያ ረቂቅ ሰነድ ፣ የክለብ አደረጃጀት ረቂቅ መተዳደሪያና መቋቋሚያ ደንብ ለይ ጉባኤው ሰፊ ውይይት በማድረግ አፅድቆታል፡፡

በሌላ በኩል በ2009 ዓ.ም የክልሎች ዕቅድ አፈፃፀም ቀርበው ውይይት የተደረገበት ሲሆን ክልሎች በአደረጃጀት ፣ በስልጠና እና በውድድር መጠናከር እንደለባቸው በጉባኤው ተጠቁመዋል፡፡

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s