​ደርቢ ዴላ ማዶኒና | ኢንተር ሚላን ከ ኤሲ ሚላን የጨዋታ ቅድመ ቅኝት

በወንደሰን ጥበቡ

በቻይናውያን ባለቤቶች የሚመሩት በመካከላቸው ቀንደኛ ተቀናቃኝነት ያለው ኢንተር ሚላን እና ኤሲ ሚላን ዛሬ (እሁድ) በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅ በሆነው የሚላን ደርቢ ጨዋታ ታለቅ ፍልሚያ ያደርጋሉ።

ኔራዙሪዎቹ በአዲሱ አሰልጣኛቸው ሉቺያኖ ስፓሌቲ እየተመሩ የውድድር ዘመኑን በመልካም ሁኔታ ጀምረዋል። ይህንን መልካም ጉዟቸውንም የማስቀጠል ውጥን ይዘውም የዛሬውን ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። ነገር ግን የቪንቼንዞ ሞንቴላው ኤሲሚላን ምንም እንኳ ከብሄራዊ ቡድን ጨዋታ በፊት በሮማ በገዛ ሜዳው 2ለ0 በሆነ ውጤት ሽንፈት ቢደርስበትም የኢንተሮችን ጉዞ ቀላል ያደርገዋል ተብሎ ግን ፈፅሞ አይጠበቅም።

የቡድኖቹ ዜናዎች

የኢንተር ሚላኑ የጨዋታ አቀጣጣይ ማርሴሎ ብሮዞቪች ለሃገሩ ክሮሺያ ባደረገው የብሄራዊ ቡድን ጨዋታ በገጠመው ጉዳት ለእሁድ ምሽቱ ጨዋታ ዝግጁ አይደለም።

በሚላን በኩል ደግሞ በቅርቡ ለክለቡ የፈረመው ቱርካዊው ሃካን ከልሃኖግሉ ክለቡ ከሮማ ጋር ባደረገው ጨዋታ ላይ በተመለከተው ቀይ ካርድ ምክኒያት ባለበት የጨዋታ ቅጣት በዚህ ጨዋታ ላይ የማይሰለፍ ተጫዋች ሲሆን፣ አንድሪያ ኮንቲ እና ሉከ አንቶኔሊ ደግሞ በጉዳት ምክኒያት በደርቢው ጨዋታ ላይ የማይሰለፉ ተጫዋቾች ናቸው።

ተከላካዩ ማቲዮ ሙሳቺዮ በልምምድ ላይ ቀላል የግጭት ጉዳት የገጠመው ቢሆንም በዚህ ጨዋታ ለሮዞኖሪዎቹ እንደሚሰለፍ ግን ይጠበቃል።

ግምታዊ አሰላለፍ

የሁለቱ ክለቦች የእርስበርስ ግንኙነት

የሚላን ደርቢ ሁለቱም ክለቦች ፈፅሞ ሽንፈት እንዲገጥማቸው የማይሹበት ጨዋታ ነው። ሁለቱ ክለቦች አንድ ስታዲየም በጋራ ይጠቀማሉ። ነገር ግን ለዚህ ጨዋታ ኢንተር ባለሜዳ በመሆኑ ከፍ ያለውን የተመልካች ቁጥር ወደሜዳ የማስገባት የመግቢያ ትኬት ዕድል አለው። በመሆኑም የሜዳ ዕድልን በመጠቀሙ በኩል የተወሰነ የዕድል ብልጫ ይኖረዋል።

የሁለቱ ክለቦችን የእርስበርስ ግንኙነት ስንመለከት ግን ኢንተር ሚላን ከፍ ያለ የማሸነፍ ብልጫ አለው። ባለፉት 20 ጨዋታዎች ኢንተር ዘጠኙን ሲያሸንፍ፣ ኤሲ ሚለን ደግሞ ስድስቱን አሸንፏል። በአምስት ጨዋታዎች ላይ ደግሞ በአቻ ውጤት ተለያይተዋል።

በጨዋታው ምን ዓይነት ውጤት ይጠበቃል?

ውጤት ወደባለሜዳው ኢንተር ሚላን እንደሚያመዝን ምንም ጥርጥር የለውም። ነገር ግን በእንደዚህ ዓይነቱ የደርቢ ጨዋታዎች ላይ ወቅታዊ ብቃትና ውጤት ሚዛን የማይደፉባቸው ብዙ አጋጣሚዎች ታይተዋል። 

ሚላን በመሃል ሜዳው ላይ ብልጫ መውሰድ የሚችል ከሆነ እና የ20 ዓመቱ ፍራንክ ኬሴ በጨዋታው ላይ ብቃቱን አጉልቶ ማሳየት የሚችል ከሆነ ሚላኖች

የማሸነፍ ዕድል የማያገኙበት ምክኒያት አይኖርም።

Advertisements
Posted in Uncategorized

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s