ህልፈት/ ኢንዶኔዢያዊው ግብ ጠባቂ ሜዳ ላይ ህይወቱ አልፏል፡፡

Image result for Indonesian goalkeeper, Choirul Huda

በእግር ኳስ ከሚከሰቱ አሳዛኝ ነገሮች አንዱ የተጫዋቾች የሜዳ ላይ ህልፈት ሲሆን በዚህ ሳምንትም ከወደ ኢንዶኔዢያ የተሰማው አሳዛኝ ዜና ቹሩል ሁዳ የተባለው ግብ ጠባቂ ከቡድን አጋሩ ጋር ሜዳ ላይ ተጋጭቶ ሕይወቱ አልፏል፡፡

ቺሩል ፔርሴላ ለተባለው ክለብ እየተጫወተ ይገኘ የነበረ ሲሆን ባሳለፍነው እሁድ በኢንዶኔዢያ  ሊግ ዋን ላይ ክለቡ ከሰሜን ፓዳንግ ጋር በነበረው ጨዋታ ከቡድን አጋሩ ጋር ተጋጭቶ ሜዳ ላይ ከወደቀ በኋላ ወደ ሆስፒታል ቢያቀናም  ግብ ጠባቂው መትረፍ ሳይችል ህይወቱ አልፋለች፡፡

የህልፈቱን ምክንያት ለሚዲያዎች ያብራሩት ግብ ጠባቂ የታከመበት ሆስፒታል ስፔሻሊስት ዶክተር ዩድስትሪዮ አንድሪ ኑግሮሆ  “ከግጭቱ በኋላ ትንፋሹ ተቋርጦ ነበር፡ ፡ የልብ ምቱም ቆሞ ነበር” በማለት ከግጭቱ በኋላ ህይወቱ ማለፉን አብራርተዋል፡፡

ግብ ጠባቂው ለፔርሴላ 500 ጨዋታዎችን ማድረግ የቻለ ሲሆን በኢንዶኔዢያ ሊግ ከሚገኙ ግብ ጠባቂዎችም ስመ ጥር እንደሆነ ተነግሯል፡፡ በርካታ የእርሱ አድናቂዎችም ከህልፈቱ በኋላ በተለያዩ መንገዶች ሀዘናቸውን ሲገልጹ ነበር፡፡ግብ ጠባቂው ህይወቱን ባጣበት ጨዋታም ክለቡ እርሱ ከሜዳ ከወጣ በኋላ ፔርሴላ ሰሜን ፓዳንግ 2-0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል፡፡

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s