ማውሪሲዮ ፓቸቲኖ፡ ማድሪድ በሮናልዶ ላይ ጥገኛ የሆነ ክለብ አይደለም

የቶተንሃሙ አሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ የፊታችን ማክኞ ከሻምፒዮኖቹ ጋር ከሚያደረጉት የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታን አስመልክተው ባደረጉት ንግግር ሪያል ማድሪድ በክርስቲያኖ ሮናልዶ ላይ ጥገኛ ያልሆነ ክለብ እንደሆነ ገልፀዋል።

ፖቸቲኖ በክርስቲያኖ ሮናልዶ ፊት አውራሪነት ቅዳሜ በላ ሊጋው ጌታፌን ማሸነፍ የቻለውን እና በተከታታት ለሁለት የውድድር ዘመናት ሻምፒዮን መሆን ከቻለው ማድሪድ ጋር ለመጫወት ወደሳንቲያጎ በርናባው ያመራሉ።

እስካሁን ካገኛቸው አራት የባሎን ዶር ሽልማቶች በተጨማሪ ዘንድሮም የማሸነፍ ዕድል እንዳለው ተስፋ የተጠለበት የማድሪድ የምንጊዜውም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪው ሮናልዶ በዚህ የውድድር ዘመን በሁሉም ውድድሮች ላይ ስድስት ግቦችን ከመረብ አሳርፏል።

ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ ግን ቶተንሃም በሪያል ማድሪዱ ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ላይ ብቻ ትኩረቱን እንደማያደርግ ተናግረዋል።

“እሱ በጣም ወሳኝ ተጫዋች ነው። ነገር ግን እነሱ [ሪያል ማድሪዶች] በጣም ብዙ ጥሩ ተጫዋቾች አሏቸው።” ሲሉ ፖቸቲኖ ለእንግሊዙ ዘ ሚረር ተናግረዋል።

“ያለቸው የተጫዋች ስብስብ የሚደንቅ ነው። እና ደግሞ በጣም ጥሩ አሰልጣኝ አላቸው። አስደናቂ ክለብ አላቸው። ነገር ግን ለዋንጫ ክብር የቡድን ስብስብህ በሙሉ አስተዋፅኦ ያስፈልግሃል።” 

“ክርስቲያኖ ሮናልዶ ልክ እንደመሲ ነው። ሁለቱም በቡድናቸው ላይ ትልቅ ተፅእኖ ያሳድራሉ። እሱ ከዓለማችን ምርጥ ተጫዋቾች መካከል አንዱ መሆኑ ግልፅ ነው።” ሲሉ ፖቸቲኖ አክለው ተናግረዋል።

“ስለነዚህ ተጫዋቾች አዲስ ነገር መናገር አስቸጋሪ ነው። ልክ እንደማራዶና ሁሉ ልዩ ናቸው።

“ጨዋታዎችን መቀየር እና ቡድናችዋን ጥሩ ማድረግ ይችላሉ። የምንጫወተው ከሪያል ማድሪድ ጋር ብቻ ሳይሆን ከዓለማችን ምርጥ ተጫዋቼች ጋር ጭምር ነው።”

ቶተንሃም እና ማድሪድ በምድብ ኤች ያደረጓቸውን የመጀመሪያ ሁለት ጨዋታዎች በማሸነፍ በእኩል ነጥብ የምድቡ የበላይ ሆነው ይገኛሉ። 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s