ዋትፎርድ አርሰናልን ባስተናገደበት ምሽት ብራዚላዊው የዋትፎርዱ መስመር ተጫዋች ሪቻርልሰን የፍጹም ቅጣት ምት ካስገኘ በኋላ ሆን ብሎ እንደወደቀ እና ቅጣት እንደሚጠብቀው ቢነገርም ከቅጣት ነጻ ሆኗል፡፡
ቪካሬጅ ሮድ ላይ የተደረገው ጨዋታ አርሰናሎች ማታ ማታ ሽንፈትን አስተናግደው ተመልሰዋል፡፡ነገርግን የመጀመሪያዋን ጎል ያስተናገዱበት መንገድ አጨቃጫቂ የነበረ ሲሆን ሪቻርልሰን ከቤለሪን ጋር ከሮጠ በኋላ ያለ ብዙ ንክኪ በመውደቁ የፍጹም ቅጣት ምት ማግኘት ችለዋል፡፡
በዚህ የፍጹም ቅጣት ምት ደግሞ አርሰናሎች ተቃውሞ ያቀረቡ ቢሆንም የእግርኳስ ማህበሩ ተጫዋቹ ላይ ቅጣት እንደሚጥል ቢጠበቅም ተጫዋቹ ግን ከቅጣት ነጻ መሆኑን ታውቋል፡፡
የቀድሞ አልቢተር ግርሀም ፖል የፍጹም ቅጣት ምቱ አግባብ እንዳልሆነ ቢናገሩም ማርክ ክላተንበርግ ደግሞ ውሳኔው ትክክል መሆኑ እና ተጫዋቹንም ለቅጣት እንደማይዳርገው ማሳወቃቸው ይታወሳል፡፡
Advertisements