ፊፋ ወቅታዊውን የዓለም ሃገራት ደረጃ ይፋ አደረገ

የዓለም የእግርኳስ አመራር አካሉ ፊፋ ኮካ ኮላ ስፖንሰር የሚያደረገውን ወቅታዊውን የዓለም ሃገራት ደረጃ ይፋ ያደረገ ሲሆን በዓለም ዋንጫ ማጣሪያው ያደረገቻቸውን ሁለት ጨዋታዎች ድል ማደርግ የቻለችው የዮኣኪም ሎዉ የዓለም ሻምፒዮኗ ጀርመንም በደረጃው አናት ላይ በቀዳሚነት መቀመጥ ችላለች።

ከቦሊቪያ ጋር አቻ የተለያየችውና ቺሊን 3ለ0 ማሸነፍ የቻለችው ብራዚል ባለፈው ወር ከነበረችበት ሁለተኛ ደረጃ አልተነቃነቀችም።

ሁለቱም ሃገራት የዓለም ዋንጫ ተሳትፎ ትኬታቸውን የቆረጡ ቢሆንም የክርስቲያኖ ሮናልዶዋ ፖርቱጋል ከሊዮኔል መሲዋ አርጄንቲና በደረጃው ቀድማ ተቀምጣለች።

ቤልጂየም ፖላንድና ፈረንሳይን አስከትላ እስከአምስት ባለው የበላይነት ደረጃ ውስጥ መግባት ችላለች።

የ2010 የዓለም ዋንጫ አሸናፊዋ ስፔን በስምንተኛ ደረጀ ላይ በመቀመጥ እስከ10 ባለው ደረጃ ውስጥ ዳግም ተመልሳ ገብታለች።

ፔሩ በ10ኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ ከአንድ እስከ10 ባለው ደረጃ ውስጥ በተደጋጋሚ የመግባት ልምድ ያላቸው እንግሊዝ በ12ኛ፣ ጣሊያን በ15ኛ እንዲሁም ሆላንድ በ20ኛ ደረጀ ላይ ለመቀመጥ ተገደዋል። 

ቱኒዚያ በሶስት ደረጃዎች ወደ28ኛ ደረጃዋን ከፍ በማድረግ ከአፍሪካ ሃገራት በቀዳሚነት ስትቀመጥ ቡርኪናፋሶን 3ለ1 በሆነ ውጤት ያሸነፈችው ደቡብ አፍሪካ ደግሞ ስድስት ደረጃዎችን በማሽሻል 74ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችላለች።

ኢትዮጵያ ደቡብ ሱዳንን እና የሰሎሞን ደሴቶችን ቀድማ ካለፈው ወር ደረጃዋ ደግሞ ሰባት ነጥቦች ዝቅ ብላ በ175ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s