ሰበር ዜና| ሼክስፒር ከሌስተር ሲቲ አሰልጣኝነታቸው ተሰናበቱ

ክሬግ ሼክስፒር ክለቡን በቋሚ አሰልጣኝነት ከያዙ አራት ወራት ጊዜ ውስጥ ከሌስተር ሲቲ አሰልጣኝነታቸው ተሰናበዋል።

የ53 ዓመቱ ሰው ክላውዲዮ ራኒየርን ተክተው ክለቡን በጊዜያዊ አሰልጣኝት የያዙት ባለፈው የውድድር ዘመን የነበረ ሲሆን፣ በዚህ ጊዜ ውስጥም ክለቡን ከወራጅ ቀጠና በማውጣት በ12ኛ ደረጃ እንዲያጠናቅቅ አድርገውት ነበር።

ይሁን እንጂ ሰኞ ምሽት ከዌስት ብሮም ጋር 1ለ1 በሆነ ውጤት በማጠናቀቃቸው በደረጃው ሰንጠረዥ ግርጌ የሚገኙት ሶስት ክለቦች አንዱ በመሆን  የደረጃ መንሸራተት በማሳየታቸው ከክለቦቹ ባለቤቶች የስንብት እጣ እንዲደርሳቸው ምክኒያት ሆኗል።

በዚህ የውድድር ዘመን አንድ ጨዋታ ብቻ ማሸነፍ የቻሉት ሌስተሮች ገና በአራት ጨዋታዎች አሰልጣኙን ፍራንክ ደቦርን ካሰናበቱት ክሪስታል ፓላሶች ቀጥለው በፕሪሚየር ሊጉ አሰልጣኘውን ለስንብት ያበቁ ሁለተኛ ክለብ ሆነዋል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s