በአዲስ አበባ እየተገነባ የሚገኘው የብሔራዊ ስታዲየም ግንባታ ሂደት ከግማሽ በላይ መጠናቀቁ ተገለፀ

የኢትዮጵያ መንግስት በአዲስ አበባ ከተማ፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ እያስገነባው የሚገኘው ብሄራዊ ስታዲየም የግንባታ ሂደት 58 በመቶ መድረሱን የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት ገልፅዋል።

ግንባታው ሲጠናቀቅ 60,000 ተመልካቾችን እንደሚይዝ የተነገረለት ግዙፉ የስታዲየም ግንባታ ሂደት በ48.8 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን፣ ስፖርታዊ ውድድሮች የሚካሄዱበት የስታዲየሙ አካልም በ95,000 ካሬ ላይ ያረፈ ነው።

በኤምኤች ኢንጂነሪንግ አማካሪነት በቻይና ስቴት ኮንስትራክሽን ኢንጂነሪንግ ሊሚትድ ኩባንያ የሚገነባው ይህ ስታዲየም ግንባታውን ለማጠናቀቅ ከተያዘለት 900 ቀናት 650 ቀናትን በስራ ላይ ውለውበታል።

የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር መረጃ የኦሎምፒክና የዓለም ዋንጫ የስታዲየም መመዘኛዎችን እንዲያሟላ ተደርጎ እየተገነባ የሚገኘው ስታዲየም የመጀመሪያ ምዕረፍ ግንባታው 2.4 ቢሊየን ብር ወጪ እንደተደረገበትና በ2010 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ ይገለፅ እንጂ አጠቃላይ የግንባታውን ወጪና ግንባታው ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ አገልግሎት ስለሚሰጥበት ጊዜ ያለው ነገር የለም።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s