ኢያን ራይት በቻምፕየንስ ሊጉ እስከ ግማሽ ፍጻሜ ሊደርሱ የሚችሉ አራት ቡድኖችን አሳወቀ

5.jpg

የቀድሞ የአርሰናል ኮከብ ተጫዋች የሆነው ኢያን ራይት በዘንድሮ የቻምፕየንስ ሊግ ውድድር ላይ ለግማሽ ፍጻሜ የሚደርሱ አራት ቡድኖች ግምቱን ሲያስቀምጥ ከአራቱ ውስጥ አንድ የእንግሊዝ ቡድን አካቷል፡፡

ጠንካራ ፉክክር እንደሚደረግበት የሚታሰበው የ 2017/2018 የአውሮፓ ቻምፕየንስ ሊግ ውድድር የአውሮፓ ሀያል ቡድኖች ከመቼውም በላይ አጓጊ ፉክክር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡

ከወዲሁም በምድብ ማጣሪያው ጠንካራ ጨዋታዎች እየተደረጉ የሚገኙ ሲሆን በጥሎማለፍ ጨዋታውም ከዋንጫ ያላነሰ ክብደት እንደሚኖራቸው የሚጠበቁ ፍልሚያዎች እንደሚኖሩ መገመቱ ከባድ አይሆንም፡፡

ከ ዘሰን ጋር ቆይታ ያደረገው ቀድሞ የአርሰናሉ ኮከብ ኢያን ራይትም የመጨረሻዎቹ አራት ውስጥ ሊገቡ የሚችሉ ቡድኖችን ግምቱን የሰጠ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ የእንግሊዙን ማንችስተር ሲቲን አካቷል፡፡

ሲቲ በእንግሊዝ ጠንካራ አጀማማር ያደረገ ሲሆን ያለው የቡድን ስብስብ እና አሰልጣኝ በቻምፕየንስ ሊጉ ላይ ከሌሎች የእንግሊዝ ቡድኖች ገፍቶ እንደሚሄድ አሳውቋል፡፡

እንደ ኢያን ራይት ግምት መሰረት ቀሪዎቹ ቡድኖች የተለመዱት ሪያል ማድሪድ እና ባርሴሎና የሚገኙበት ሲሆን ኔይማርን ማዘዋወር የቻለው ፓሪስ ሴንት ጄርሜይንም ሌላኛው ቡድን አድርጎ አካቶታል፡፡

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s