የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ቅድመ ቅኝት

የሻምፒዮንስ ሊጉ ሶሰተኛ የምድብ ጨዋታዎች በተለያዩ የአውሮፓ ሃገራት ዛሬ እና ነገ ምሽት ይካሄዳሉ። ዛሬ ምሽት ስምንት ጨዋታዎች የሚደረጉ ሲሆን ከምሽቱ ጨዋታዎች አበይት ናቸው ያልናቸውን ጨዋታዎች ግምታዊ አሰላለፎች፣ የቡድኖቹ ወቅታዊ ዜናዎች እና ሌሎች ቁጥራዊ መረጃዎችንም አክለን እንደሚከተለው ቃኝተናቸዋል።

ሪያል ማድሪድ ከ ቶተንሃም

ያደረጓቸውን የመጀመሪያ ሁለት ጨዋታዎች በማሸነፍ በተመሳሳይ ስድስት ነጥብ ምድብ ኤችን የሚመሩት ሁለቱ ክለቦች ዛሬ ምሽት በሳንቲያጎ በሚያደረጉት ጨዋታ የምድቡ የበላይ ለመሆን ይፋለማሉ። 

ሪያል ማድሪድ በጉዳት እና በህመም ምክኒያት ጋርዝ ቤልን፣ ዳኒ ካርቫኻልና ማቲዮ ኮቫቺችን በዚህ ጨዋታ ላይ አያሰልፍም።

ቪክቶር ዊኒያማ ቶተንሃም በሳምንቱ መጨረሻ በፕሪሚየር ሊጉ ሊቨርፑል ሲገጥም ወደሜዳ የሚመለስ ቢሆንም፣ በዚህ ጨዋታ ላይ ግን የማይሰለፍ ተጫዋች ነው። ዴሌ አሊ አሁንም በዚህ ጨዋታ በቅጣት ምክኒያት የማይሰለፍ ይሆናል።

ዳኒ ሮዝ እና ሞሳ ዴምቤሌ ከቡድኑ ጋር ወደስፔኗ ዋና ከተማ የተጓዙ ቢሆንም፣ የመሰለፍ ዕድል ያለው ግን ዴምቤሌ ብቻ ነው። ዳኒ ሮዝ ከኤሪክ ላሜላ ጋር ከጉዳት ወደልምምድ የተመለሰው በቅርብ ጊዜ በመሆኑ ለዚህ ጨዋታ በሙሉ ብቃት ላይ አይገኝም።

ቤን ዴቪስ በህመም ምክኒያት በዚህ ጨዋታ ላይ የመሰለፉ ነገር እርግጥ ያልሆነ የለንደኑ ክለብ ተጫዋች ነው።

ማንችስተር ሲቲ ከ ናፖሊ

የፔፕ ጋርዲዮላው ማንችስተር ሲቲ በሁሉም ውድድሮች ላይ ያሳኳቸውን ድሎች 10 የማድረስ ውጥን ይዞ በሻምፒዮንስ ሊጉ በኢትሃድ ስታዲየም የጣሊያኑን ክለብ ናፖሊን ይገጥማል።

ናፖሊም በሴሪ ኣው በተከታታይ ስምንት ጨዋታዎችን የማሸነፍ ሪከርድ ይዞ እና የሴሪ ኣው መሪ በመሆን ወደእንግሊዝ የሚያመራ ቢሆንም፣ በሻምፒዮንስ ሊጉ ምድብ ኤፍ ላይ ግን በሶስት ነጥቦች ዝቅ ብሎ ፉክክሩን እያደረገ ይገኛል።

ሰርጂዮ አግዌሮ በሆላንድ በመኪና አደጋ ምክኒያት ከገጠመው የጎድን አጥንት ጉዳት ይመለሳል ተብሎ ከተጠበቀው ጊዜ ፈጥኖ ወደሜዳ ቢመለስም በቅዳሜ ጨዋታ ግን ግልጋሎት ያልሰጠ ተቀያሪ ተጫዋች ነበር።

ቤንጃሚን ሜንዲ በቁርጭምጭሚት ጉዳት ለረዥም ጊዜያት ከሜዳ ርቆ የሚቆይ ሲሆን፣ አምበሉ ቪንሰንት ኮምፓኒም እስከሁን ወደጨዋታ ለመመለስ ዝግጁ ያልሆነ ተጫዋች ነው።

በእንግዳው ቡድን በኩል ፓላንዳዊው አጥቂ አርካዲስ ሚሊ በረጅም ጊዜ የጉልበት ጉዳት ምክኒያት በዚህ ጨዋታ ላይ የማይሰለፍ ብቸኛ ተጫዋች ነው።

ማሪቦር ከ ሊቨርፑል

የየርገን ክለፑ ሊቨርፑል በምድብ ኢ ባዳረጋቸው የመጀመሪያ ሁለት የምድቡ ጨዋታዎች መሰብሰብ የቻለው ሁለት ነጥቦችን ብቻ ነው። ነገር ግን ወደስሎቫኒያ አምርቶ በስተዲዮን ሊዩድስኪ በሚያደርገው በዛሬው ጨዋታ የሚያገኘው ድል ወደቀጣዩ ዙር ለማለፍ መደላድልን ይፈጥርለታል።

ቀዮቹ በቋንጃ ገዳት ለስድስት ሳምንታት ከሜዳ የሚርቀውን ሳዲዮ ማኔን፣ እና በጉዳት ላይ የሚገኙትን አዳም ላላና እና ናትናኤል ክላይንን በዚህ ጨዋታ ላይ አያሰልፏቸውም።

በተከታታይ የሁለት ዓመታት የስሎሻኒያ ሻምፒዮኑ ማሪቦር ወደሲቪያ አምርተውና በሜዳቸው በስፓርታክ ሞስኮ ከገጠማቸው አስቸጋሪ ውጤት በማንሰራራት ወቀጣዩ የጥሎ ማለፍ ዙር ለማለፍ ከመርሲሳይዱ ክለብ ጋር በሜዳቸው የሚያዳረጉትን ጨዋታ በውጤት ማጠናቀቅ የግድ ይላቸዋል።

በሌሎች የዛሬ ምሽት ጨዋታዎች ስፓርተክ ሞስኮ ከ ሲቪያ፣ ፌይኑርድ ከሻካታር ዶኔትስክ፣ ሞናኮ ከቤሽኪታሽ፣ አርቢ ሌፕዚግ ከፖርቶ እንዲሁም አፖል ኒኮሲያ ከዶርትሙንድ በተመሳሳይ 3፡45 ላይ ይጫወታሉ። 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s