የክሪስታል ፓላሱ ደጋፊ አስገራሚ የውሎ ማስታወሻ

ሰባት ጨዋታዎች፣ ዜሮ ግብ፣ ዜሮ ነጥብ። የክሪስታል ፓላሶች የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የዚህ የውድድር ዘመን ጅማሮ ነበር። ነገር ግን ባለፈው ቅድሜ የእግርኳሱን ዓለም በእጅጉ ባስገረመ ሁኔታ ሻምፒዮኑን፣ ቼልሲን 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል። 

ክለቡ ይህን ሁሉ ውጤት ሲያስመዘግብ ቤን ሚንትራም የተሰኘው የ25 ዓመቱ የፓላስ ደጋፊ የክለቡን እያንዳንዱን ጨዋታ በስታዲየም ተገኝቶ በመታደም ለክለቡ ያለውን ታማኝነት ማሳየት ችሏል።

ደጋፊውም ይህን ልብ የሚነካ ክለቡን ለመደገፍ ያሳየውን ፍቅር በግል የውሎ ማስታወሻው ላይ እንደሚከተለው አስፍሯል።

“ቡድኔ ለአምስት ወራት ያለግብ ከተጓዘበት ጊዜ አንስቶ በግቦች መጨፈር ምን ያህል እወድ እንደነበር መረዳት አልቻልኩም።

“ክሪስታል ፓላስ በሜዳው ሲጫወትም ሆነ ከሜዳው ውጪ  ወደሚጫወትበት ሁሉ እሄዳለሁ። የዚህን የውድድር ዘመን አንድ ጨዋታ እንኳ አላሳለፍኩም። ለማንኛውም ግን እስከቅዳሜው ጨዋታ ድረስ ያደረጉት ጨዋታ በጣም ህመም እንደነበር መናገር ተገቢ ነው።

“የመጀመሪያውን የፕሪሚየር ሊግ ግብ ለመመልከት 641 ደቂቃዎችን ጠብቄያለሁ። ከዚያ ግን በአንድ ጨዋታ ሁለት ግቦችን አየሁ። ለጥበቃዬም ጥሩ ክፍያ አገኘሁ።

“የእግርኳስ ቡድኑን ለመመልከት በመቶዎች የሚቆጠሩ ፓውንዶችን ወጪ አድርጌ እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ማይልሶችን መጓዜ ሰዎች እብድ አድርገው ሊያስቡኝ እንደሚችሉ አውቃለሁ።

“ሁሉም ሰው ይህን እንዲረዳ አልጠብቅም። ነገር ግን ሌላ አይነት መንገድ አልነበረኝም። ወደፓላሦች አምርቶ እነሱን መመልከት ሱስና የህይወቴ አንዱ አካል ሆኗል።

“ማንችስተር ዩናይትድን እና ሊቨርፑል የሚደግፉ አንዳንድ በለንደን የሚኖሩ ደጋፊዎች አውቃለሁ። ነገር ግን ቡድናቸው ሲጫወት የሚመለከቱት በቴሌቪዥን ነው። ይህንን ከዚያ ጋር ላወዳድረው አልችልም።

“በፓላስ ከቡድኑ ጋር እውነተኛ ቁርኝት እንዳለኝ እና በሜዳው ላይ የሚሆነው ነገር አንድ አካል እንደሆንኩ ይሰማኛል። ደጋፊዎች አንዳች ተጨባጭ ልዩነት መፍጠር ይችላሉ። በየሳምንቱ ከተጫዋቾች ጀርባ መሆንን እንድወድ የሚያደረግኘም ይኸው ነው።

“በአሁኑ ጊዜ በህይወቴ ላይ አብይ የሚባል ኃለፊነት የለብኝም። ስለዚህ አብዛኛውን ህይወቴን ለዚህ አውላለሁ። አንድ ቀን ልጆች ሊኖሩኝ እና ይህን ማድረግ አልችል ይሆናል። ስለዚህ በየሳምንቱ የማነሳው ጥያቄ ወደጨዋታው እሄድ ይሆን ሳይሆን እንዴት ወደጨዋታው እገባለሁ የሚል ነው። 

“ከሰባት ዓመት ዕድሜዬ አንስቶ ፓለሶችን ስመለከተላቸው ኖሬያለሁ። ስለዚህ የሚፈጠረውን ነገር እንዴት ማስተናገድ እንዳለብኝ ተለማምጃለሁ። ነገር ግን በፕሪሚየር ሊጉ ታሪካችን ሁሉ የከፋውን ጅማሮ አያለሁ ብዬ እንዳልጠበቅኩ ማመን ይኖርብኛል። 

“ሰባት ጨዋታዎችን አድርገናል። በሁሉም ከመሸነፋችንም በላይ አንድ ግብ እንኳ ማስቆጠር አልቻልንም። ጥሩ የውድድር ዘመን እንዲኖረን መጠበቄ ግን አስቂኝ ነገር ነው።”

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s