“ሁላችንም ሊዮ ሜሲ የአለማችን ምርጥ ተጫዋች እንደሆነ እናውቃለን” – ኤርኔስቶ ቫልቬርዴ

lionelmessi-cropped_1ojkt3s2iih4k16j0nirclpy2g.jpg

ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከሊዮ ሜሲ ጋር ለአምስተኛ ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊ በመሆን ሪከርዱን እንደሚጋራ በሚጠበቅበት አመት የባርሴሎናው አሰልጣኝ ኤርኔስቶ ቫልቬርዴ ከሁለቱ የተሻለው ተጫዋች ለሁላችንም ግልጽ ነው ሲሉ ለሊዮ ሜሲ ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል፡፡

ሁለቱ ኮከቦች ባለፉት ተከታታይ አመታት በአጠቃላይ ለዘጠኝ ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊ መሆን ችለዋል፡፡ይህ የበላይነታቸውም በቀጣዩ አመታት እንደሚቀጥል የሚጠበቅ ሲሆን ዘንድሮ ለአምስተኛ ጊዜ ሮናልዶ በማሸነፍ ከሊዮ ሜሲ ጋር እንደሚስተካከል ይጠበቃል፡፡

የሁለቱ ተጫዋቾች ፉክክር በመቀጠል በተራው ደግሞ ሊዮ ሜሲ ድንቅ አጀማመር በመጀመር በላሊጋው ከወዲሁ ጎል ማምረቱን ተያይዞታል፡፡ይህ ደግሞ በቀጣይ አመታትም የሁለቱ ተጫዋቾች ፉክክር እንደሚቀጥል አስተያየት የሚሰጡ አልጠፉም፡፡

እንደ ወቅቱ የባርሴሎና አሰልጣኝ ኤርኔስቶ ቫልቬርዴ ሀሳብ ግን ከሁለቱ የተሻለ ተጫዋች ማን እንደሆነ ለመለየት ምንም የሚያጠራጥር ነገር አለመኖሩን ተናግረዋል፡፡

“ሁሉም ሰው ሊዮ ሜሲ የአለማችን ምርጥ ተጫዋች እንደሆነ ያውቃል፡፡ባሎንዶርም ማንም ያግኝ ማንም ሀሳቤን አያስቀይርም፡፡ሁላችንም ምርጡ ማን እንደሆነ እናውቃለን፡፡” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ሜሲ ዘንድሮ በሁሉም ውድድር ላይ ለባርሴሎና 12 ጨዋታዎችን ተጫውቶ 14 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s