ማን ሲቲ ከወዲሁ የፕሪሚየር ሊጉን የግብ ክብረወሰን ሊሰብር የሚችልበት ጉዞ እያደረገ ይገኛል 

በፕሪሚየር ሊጉ የመጀመሪያዎቹ ስምንት ጨዋታዎች 29 ግቦችን ማስቆጠር የቻለው የፔፕ ጋርዲዮላው ቡድን ከወዲሁ ማንችስተር ሲቲ የካርሎ አንቸሎቲው ቼልሲ ማስቆጠረ ከቻላቸው እና በፕሪሚየር ሊጉ ክብረወሰን ሆኖ የቆየውን 103 ግብ መላቅ የሚችልበት አቋም ላይ ይገኛል።

ስቶክ ሲቲን ባለፈው ቅዳሜ 7ለ2 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት ማሸነፍ የቻለው ሲቲ በዚህ የውድድር ዘመን በፕሪሚየር ሊጉ ያደረጋቸውን ግቦች ከዚህ ቀደም በ206/07 አጠቃላይ የውድድር ዘመን ማስቆጠር ከቻለውም በላይ 29 ሊያደርስ ችሏል። 

በእንግሊዝ ቀዳሚ ሊግ በውድድር ዘመኑ የመጀመሪያዎቹ ስምንት ጨዋታዎች ይህን ያህል በርከታ ግቦችን ማስቆጠር የቻለው ክለብ ኤቨርተን ነበር። የመርሲሳይዱ ክለብ በ1894/95 የውድድር ዘመን 30 ግቦችን አስቆጥሯል።

ሲቲ በየጨዋታው እያስቆጠራቸው የሚገኙትን 3.63 የግብ መጠን በዘላቂነት የሚቀጥልበት ከሆነ በውድድር ዘመኑ መጨረሻ የሚያስቆጥራቸው አጠቃላይ ግቦች 138 ይደርሱለታል። ይህ ማለት ደግሞ ቼልሲ በ2009/10 የውድድር ዘመን ያስቆጠራቸውን 103 የሊጉ ክብረወሰን የሆኑ ግቦችን ሊበልጥ ይችላል።

ገና 30 ጨዋታዎች በቀሩት የፕሪሚየር ሊጉ የውድድር ዘመን ሲቲ የቼልሲን ክብረወሰን መስበር የሚችልበት ይዞታ ላይ ያለ ይመስላል

ይህን የግብ ክበረወሰን እስከሁን የያዘው የካሮ አንቸሎቲው ቼልሲ አሁን ሲቲ በሚገኝበት የስምንት ጨዋች ጊዜ ማስቆጠር የቻለው 18 ግቦችን ብቻ ነበር።

ከቼልሲ በተጨማሪ በፕሪሚየር ሊጉ ከ100 በላይ ግቦችን ማስቆጠር የቻሉ ሌላ ሁለት የሊጉ ክለቦች ማን ሲቲና ሊቨርፑል ነበሩ። ሁለቱም ይህን ግብ ያስቆጠሩት በ2013/14 የውድድር ዘመን የነበረ ቢሆንም፣ ከስምንተኛው ጨዋታ በኋላ ማስቆጠር የቻሉት ግብ አሁን ሲቲ ማስቆጠር ከቻለው ዝቅ ያለ ነበር። በወቅቱ ሲቲ 20 ግቦችን ሲያስቆጥር ፣ ሊቨርፑል ደግሞ ያስቆጠረው 13 ግቦችን ነበር።

በ2011/12 የውድድር ዘመን ማን ሲቲ ከስምንት ጨዋታዎች በኋለ 27 ግቦችን ከመረብ ላይ አሳርፎ የነበረ ቢሆንም፣ የውድድ ዘመኑን ያጠናቀቀው ግን በአጠቃላይ 93 ግቦችን በማስቆጠር ነበር። የሊጉን ዋንጫ ለማንሳትም በተመሳሳይ የግብ ቁጥር የውድድር ዘመኑን ካጠናቀቀው የማንችስተር ከተማ ተቀናቃኙ ለመብለጥ የግብ ልዩነት አስፈልጎት ነበር።

በ2004/05 አርሰናል በስምንተኛው ሳምንት 26 ግቦችን ከመረብ ላይ አሳርፎ የነበረ ቢሆንም በቀሪዎቹ 30 ጨዋታዎቹ ግን ማስቆጠር የቻለው ተጨማሪ ግቦች 60 ነበሩ። 

ነገር ግን የታሪክ ግጥጥሞሹ ለፔፕ ጋርዲዮላው ቡድን መልካም ዕድልን ይዞለት የሚመጣ ይመስላል። ስቶክ ሲቲ ለመጨረሻ ጊዜ በሰባት ግብ መሸነፍ የቻለው እ.ኤ.አ. በ2010 የሊጉን አጠቃላይ ከፈተኛ የግብ ክበረወሰን በያዘው ቼልሲ ነበር።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s