ሲቲ ካፕ/ ቅዱስ ጊዮርጊስ ለፍፃሜ ያለፈበትን ውጤት አስመዘገበ

ወደወሳኝ ምህራፍ የተሻገረው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ (ሲቲ ካፕ) ዛሬ በግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ሲቀጥል የአራት ጊዜው የውድድሩ አሸናፊ ቅዱስ ጊዮርጊስ ለአምስተኛ ሻምፒዮንነቱ የተንደረደረበትን ውጤት አስመዝግቧል፡፡

ምድብ “ለ”ን በአንደኝነት ያጠናቀቀው ቅዱስ ጊዮርጊስንና ምንብ “ሀ”ን በመሪነት የጨረሰው ጅማ አባጅፋርን ያገናኘው የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ በደማቅ የደጋፊዎች ድባብ ታጅቦ መደበኛው የጨዋታ ክፍለጊዜ ያለጎል በአቻ ውጤት የተጠናቀቀ ሲሆን አሸናፊውን ለመለየት ወደመለያ ምት ለማምራት ተገዷል ፤ በዚህም መሰረት ፈረሰኞቹ 4-2 በማሸነፍ የፊታችን እሁድ ለሚካሄደው የፍፃሜ ፍጥጫ ማለፍ ችለዋል፡፡

የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የጨዋታው ኮከብ ለሆኑ ተጫዋቾች የሚሰጠውን ሽልማት የጅማ አባጅፋሩ ዮናስ ገረመው ማግኘት ችሏል፡፡

በነገው ዕለት ሁለተኛውን የፍፃሜ ተፋላሚ ለመለየት የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ የሚደረግ ሲሆን የምድብ “ሀ” አንደኛ የሆነው ኢትዮጵያ ቡና ምድብ “ለ” በሁለተኝነት ካጠናቀቀው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ይፋለማል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s