የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ቅድመ ቅኝት

የሻምፒዮንስ ሊጉ ሶሰተኛ የምድብ ጨዋታዎች በተለያዩ የአውሮፓ ሃገራት ዛሬ ምሽት ስምንት ጨዋታዎች የሚደረጉ ሲሆን ከእነዚህ ጨዋታዎችም አበይት ናቸው ያልናቸውን ጨዋታዎች ግምታዊ አሰላለፎች፣ የቡድኖቹ ወቅታዊ ዜናዎች እና ቁጥራዊ መረጃዎችንም አክለን እንደሚከተለው ቃኝተናቸዋል።

ቼልሲ ከ ሮማ

በዋንዳ ሜትሮፖሊታኖ አትሌቲኮ ማድሪድን ባለፈው የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ሪያል ማድሪድን 2ለ1 በማሸነፍ የምድባቸው ቀዳሚ የሆኑት ሰማያዊዎቹ በሶስተኛው የምድብ ጨዋታቸው ደግሞ በስተንፎርድ ብሪጅ ዛሬ ምሽት የጣሊያኑን ክለብ ሮማን ይገጥማሉ።

ሮማ ኤፍሲ ካራባግብ በማሸነፍና ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር በአቻ ውጤት ተለያይቶ ከምድቡ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ወደለንደን በመጓዝ ይህን ጨዋታ የሚያደርግ ይሆናል።

ቼልሲ በጉዳት ላይ የሚገኙትን ንጎሎ ካንቴን እና ዳኒ ድሪንክዋተርን በዚህ ጨዋታ ላይ አያሰልፉም።

ሰማያዊዎቹ ቅዳሜ በፕሪሚየር ሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ግርጌ ላይ በሚገኘው ክሪስታል ፓላስ ሽንፈት ሲደርስባቸው ቪክቶር ሞሰስን በጨዋታው በጉዳት አጥተውታል።

ይሁን እንጂ አንቶኒዮ ኮንቴ ከነበረበት ጉዳት ወደልምምድ የተመለሰውን አልቫሮ ሞራታን በተመለከተ መልካም ዜና አላቸው። 

በሮማ በኩል አሰልጣኙ ኢዩሴቢዮ ዲ ፍራንሴስኮ በሳምንቱ መጨረሻ ከናፖሊ ጋር በተደረገው ጨዋታ ጉዳት የገጠመው ኮስታስ ማኖላስ በዚህ ጨዋታ ላይ እንደማይሰለፍ ገልፀዋል።

እንዲሁም እንግዳው ቡድን ፓትሪክ ሺክን፣ ግሪጎር ደፍረልን እና ኤመርሰንን ፓልሜሪን አያሰልፍም ተብሎ ሲጠበቅ፣ ስቴፈን ኤል ሻራዋይ እና ኬቨን ስትሩትማንም መሰለፋቸው አጠራጣሪ ነው።

ቤኔፊካ ከ ማንችስተር ዩናይትድ

ማንችስተር ዩናይትድ በምሽቱ ጨዋታ ወደፖርቱጋል ተጉዞ የሻምፒዮንስ ሊግ የተሳካ ጉዞውን ለማስቀጠል ይጫወታል።

አንድሬ አልሜዳ ቤኔፊካ በባሰል 5ለ0 በሆነ ውጤት በደረሰበት ከባድ ሽንፈት ቀይ ካርድ መመልከቱን ተከትሎ በዚህ ጨዋታ በቅጣት ምክኒያት አይሠለፍም። 

ዩናይትድ ደግሞ በጉዳት ላይ የሚገኙትን ፖል ፖግባ፣ ዝላታን ኡብራሂሞቪችንና በብሄራዊ ቡድን ጨዋታ ላይ ጉዳት የገጠመውን ማሩዋን ፌላይኒን በዚህ ጨዋታ ላይ አያሰልፍም። 

ሉኬ ሻው ከዌስትሀም አቻው ጋር አሁድ ዕለት ከተጫወተው ከ23 በታች ቡድኑ ውስጥ ተሰልፎ መጫወት ችሏል። ይሁን እንጂ የመስመር ተከላካዩ የተሟላ የጨዋታ አቋም ላይ እስኪገኝ ድረስ በዋናው ቡድን ውስጥ ይጫወታል ተብሎ አይጠበቅም።

ባርሴሎና ከ ኦሎምፒያኮስ

ባርሴሎና በምሽቱ ጨዋታ ኦሎምፒያኮስን በኑ ካምፕ በማሸነፍ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ዙርን ለመቀላቀል ይችላል። 

ባሉኣግራናዎቹ ከጁቬንቱስና ከስፖርቲንግ ጋር ያደረጓቸውን ሁለት የመጀመሪያ የሻምፒዮን ሊግ ጨዋታዎች በአስደናቂ ሁኔታ ድል ማድረግ ችለው ስድስት ነጥቦችን ሰብስበዋል። 

በሌላ በኩል ኦሎምፒያኮስ እስካሁን ያደረጓቸውን ሁለቱንም ጨዋታዎች በሽንፈት በማጠናቀዋቸው በሻምፒዮንስ ሊጉ ችግር ውስጥ ይገኛሉ። በመሆኑም የምድቡ ተስፋቸውን ለምለምለም በኑ ካምፕ አንዳች ውጤት ይዘው መመለስ ይጠበቅባቸዋል። 

የባርሴሎናው አሰልጣኝ ኤርነስቶ ቫልቬርዴ ቅዳሜ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር በአቻ ውጤት ከተለያዩ በኋላ አዲስ የሚባል ጉዳት በቡድናቸው ውስጥ የለም። የረጅም ጊዜ ጉዳት ሰለባ የሆኑት ራፊንሃ፣ ኦስማን ዴምቤሌ እና አርዳ ቱራን ግን በዚህ ጨዋታ ላይ የማይሰፉ ተጫዋቾች ናቸው።

የኦሎምፒያኮሱ አሰልጣኝ ታኪስ ለሞኒስ ከዚህ ጨዋታ በፊት ብዙ የጉዳት ችግሮች የሉባቸውም። ብቸኛው የቡድናቸው የጉዳት ሰለባ የዳሌ ጉዳት የገጠመው ፋርዱ ናቡሃኔን ብቻ ነው።

በሌሎች የዛሬ ጨዋታዎች ሲኤስኬኤ ሞስኮ ከባሰል፣ አንደርሌክት ከፒኤስጂ፣ ባየር ሙኒክ ከሴልቲክ፣ ጁቬንቱስ ከስፖርቲንግ በተመሳስይ ሰዓት ምሽት 3፡45 ላይ ሲጫወቱ፣ ካራባግ እና አትሌቲኮ ማድሪድ የሚያደረጉት ጨዋታ ደግሞ ቀደም ብሎ ምሽት 1 ሰዓት ላይ ይደረጋል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s