“ራሱን መለስ ብሎ መመልከት መጀመር የሚኖርበት ይመስለኛል።” ሲሉ ኮንቴ ለሞሪንሆ ምላሽ ሰጡ 

የቼልሲው አልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ የማንችስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ ሆዜ ሞሪንሆ ስለሰማያዊዎቹ ተጫዋቾች ከመጨነቅ ይልቅ ስለራሰቸው ተጫዋቾች መጨነቅ እንደሚገባቸው ተናግረዋል።

ኮንቴ በሻምፒዮንስ ሊጉ ረቡዕ ምሽት ከሮማ ጋር ባደረጉት ጨዋታ 3ለ3 በሆነ አቻ ውጤት ከመለያየታቸው በፊት በቡድን ስብስባቸው ውስጥ በርካታ ጉዳቶች እንዳሉባቸው ገለፀው ነበር።

ትናንት ምሽት ዩናይትድ ቤኔፊካን 1ለ0 ማሸነፉን ተከትሎ ሞሪንሆ በጉዳት ጉዳይ የሚነጫነጩ አሰልጣኞችን ሸንቆጥ አድርገዋል።።

“እኔ ፈፅሞ ስለጉዳት አልናገርም።” በማለት ፖርቱጋላዊው አሰልጣኝ ተናግረው “ሌሎች አሰልጣኞች ግን አንድ ተጫዋች ሲጎዳባቸው [ስራቸው] ማልቀስ፣ ማልቀስ፣ ማልቀስ ነው።” ሲሉ ገልፀዋል።

በዚህ ንግግር ደስተኛ ያልሆኑት አንቶኒዮ ኮንቴም ፓርቱጋላዊው ታክቲሺያን ስለቀድሞው ክለባቸው ያላቸውን ጭንቀት እንዲያቆሙ ተናግረዋል።

“ስለሌሎች ሳይሆን ስለራሱ ቡድን መጨነቅ እና ራሱን መለስ ብሎ መመልከት መጀመር የሚኖርበት ይመስለኛል።” በማለት ጣሊያናዊው አሰልጣኝ ተናግረዋል።

ምን ለማለት ፈልገው እንደሆነ ለቀረበላቸው ጥያቄም “ሞሪንሆ በቼልሲ ስለሆነው ነገር መመልከት የሚችሉበት ብዙ ጊዜ የነበራቸው ይመስለኛል።” በማለት ምለሽ ሰጥተዋል። አክለውም “ያለፈውን የውድድር ዘመን ጨምሮ ብዙ ጊዜ ነበራቸው።” ሲሉ ገልፀዋል።

ንጎሎ ካንቴ፣ ዳኒ ድሪንክ ዋተር እና ቪክቶር ሞሰስ በጉዳት ምክኒያት በምሽቱ ጨዋታ ላይ መሰለፍ ያልቻሉ ተጫዋቾች የነበሩ ሲሆን፣ ዴቪድ ልዊዝ (የባት) እና ቲሞ ባከዮኮ (የብሽሽት) በሮማው ጨዋታ ላይ ጉዳት የገጠማቸው ተጫዋች ናቸው። 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s