ራባህ ማጀር በድጋሚ የአልጄሪያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ተደርገው ተሾሙ

የአልጄሪያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የ58 አመቱን ራባህ ማጀር አዲሱ የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ አድርጎ መቅጠሩን አሳወቀ።ለ2018 የአለም ዋንጫ መሳተፍ ያልቻለው እና በማጣሪያው ደካማ የነበረው የአልጄሪያ ብሔራዊ ቡድን ስፔናዊው ሉካስ አልካራዝን ማሰናበቱ ይታወሳል።

በተለይ በማጣሪያው አንድ ነጥብ ብቻ በማስመዝገብ የምድቡን የመጨረሻ ደረጃ ላይ በመቀመጡ አሰልጣኙ ከስድስት ወራት ቆይታ በኋላ ከሀላፊነታቸው እንዲነሱ ምክንያት ሆኗል።

የእግርኳስ ፌዴሬሽኑ በምትኩ ራባህ ማጀርን አሰልጣኝ አድርጎ መቅጠሩን ይፋ አድርጓል።አሰልጣኙም ባለፉት ሶስት አመታትን ብሄራዊ ቡድኑን የሚያሰለጥኑ አምስተኛው አሰልጣኝ ሆነዋል።

በ1987 የአፍሪካ የአመቱ ምርጥ ተጫዋች የተባሉት ራባህ ማጀር “የበረሀ ቀበሮዎቹን” ከዚህ ቀደም ለሶስት ጊዚያት ያህል ማሰልጠን ችለው ነበር።

በ 1993፣በ1999 እና በ2002 ብሄራዊ ቡድኑን ማሰልጠናቸው ይታወሳል።2002 ላይ ለመጨረሻ ጊዜ ቡድኑን ሲያሰለጥኑ ከአፍሪካ ዋንጫ በጊዜ በመሰናበታቸው ከሀላፊነታቸው እንዲነሱ ተደርገው ነበር።

አሰልጣኙ የመጀመሪያ ጨዋታቸውም ከናይጄሪያ ጋር ለአለም ዋንጫ ማጣሪያ ሲሆን ቀደም ብለው በመውደቃቸው ጨዋታው የመርሀግብር ከማሟላት ያለፈ ትርጉም አይኖረውም።

ነገርግን ብሔራዊ ቡድኑን በ 2019 የካሜሮን የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ማሳተፍ የመጀመሪያ የቤት ስራቸው እንደሚሆን ይጠበቃል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s