ሲቲ ካፕ/ ኢትዮጵያ ቡና ወደፍፃሜ አለፈየመጨረሻው ምህራፍ ላይ የደረሰው የአዲስ አበባ ዋንጫ ዛሬ ሁለተኛውን የፍፃሜ ፍልሚያ ያደረገ ሲሆን ኢትዮጵያ ቡና ወደፍፃሜው በማለፍ የሸገር ደርቢን እውን አድርጓል፡፡

እጅግ ደማቅ የደጋፊ ድባብን ያስተናገደው ጨዋታ ቡናማዎቹን ባለድል ሲያደርግ የጨዋታውን ብቸኛ ጎል የቡድኑ አማካይና አምበል ተወዳጁ መስኡድ መሃመድ አስቆጥሯል፡፡ 

ይህን ተከትሎም ኢትዮጵያ ቡናና ቅዱስ ጊዮርጊስ የፊታችን እሁድ ለሚደረገው የፍፃሜ ጨዋታ በሸገር ደርቢ የሚፋጠጡ ይሆናል፡፡

በአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሚሰጠውን የኮከብ ተጫዋችነት ሽልማት ጎል አስቆጣሪው መስኡድ ተሸልሟል፡፡

ውድድሩ የፊታችን እሁድ በአዲስ አበባ ስታዲየም በሚደረገው ጨዋታ ፍፃሜውን ሲያገኝ በ 8:00 ሰዓት ኢትዮ ኤልክትሪክ ከ ጅማ አባጅፋር ጋር የደረጃ ጨዋታውን የሚያደርግ ሲሆን 10:00 ላይ ኢትዮጵያ ቡናና ቅዱስ ጊዮርጊስ የ2010 የአዲስ አበባ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታን ያደርጋሉ፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s