ለመሀመድ ሳላህ የቀረበው ባለቅንጦት ስጦታ!

ግብጽ ከ 27 አመት በኋላ ወደ አለም ዋንጫ እንድትመለስ ትልቅ ሚና የተጫወተው የሊቨርፑሉ የመስመር አጥቂ መሀመድ ሳላህ ለሀገሩ ለሰራው ክብር በመስጠት ከአንድ ግብጻዊ ባለሀብት የቀረበለት የቅንጦት ስጦታ ሳይቀበል ቀረ።

ለ 2018 የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ከጋና፣ኮንጎ እና ዩጋንዳ ጋር የተደለደለችው ግብጽ አንድ ጨዋታ እየቀራት ወደ አለም ዋንጫ የሚወስዳትን ትኬት መቁረጥ ችላለች።

ከምድቧ ሽንፈት ያልቀመሰችው ግብጽ ከሳምንት በፊት ከኮንጎ ጋር ያደረገችው የሜዳዋን ጨዋታ 2-1 በማሸነፍ ህልሟን አሳክታለች።

ለዚህ ክብር እንድትበቃ ደግሞ በእለቱ የአንበሳውን ድርሻ የወሰደው የሊቨርፑሉ አጥቂ መሀመድ ሳላህ ነው።

ሳላህ ኮንጎ ላይ ሁለቱንም ጎል ማስቆጠር የቻለ ሲሆን በተለይ 95ኛ ደቂቃ ላይ ያስቆጠራት የፍጹም ቅጣት ምት ግብጻዊያንን በደስታ ያሰከረች ነበረች።

አገሩን ለአለም ዋንጫ በማሳለፍ የጀግንነት ስራን የሰራው ሳላህ ብዙ ሙገሳዎች እየቀረቡለት የሚገኝ ሲሆን በተወለደበት ከተማም የሚገኘው የተጫዋቹ የድሮ ትምህርት ቤት ስያሜውን በመቀየር በመሀመድ ሳላህ ስም እንዲጠራ ተወስኗል።

አሁን ደግሞ ከአንድ ግብጻዊ ባለሀብት የቀረበለት ዘመናዊ የተቀናጣ ቪላ ቤት ስጦታ ሳይቀበል ቀርቷል።

ሳላህ በምትኩ ለትውልድ መንደሩ እርዳታ ቢደረግ እንደሚየስደስተው ለባለሀብቱ በማሳወቅ ስጦታውን ሳይቀበል ቀርቷል። 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s