ሜሱት ኦዚል ወደ ማንችስተር ዩናይትድ እንደሚያቀና ለቡድን ጓደኞቹ ተናገረ

ሚረር ጋዜጣ በዛሬ[አርብ] እትሙ በጀርባ ገጹ ላይ በሜሱት ኦዚል የአርሰናል ቆይታ ዙሪያ ለመድፈኞቹ አስደንጋጭ መረጃ ይዞ ወጥቷል።

ጀርመናዊው የቀድሞ የሪያል ማድሪድ የአጥቂ አማካይ ከአርሰናል ጋር ያለውን ኮንትራት በአመቱ መጨረሻ ላይ ይጠናቀቃል።

አርሰናል የተጫዋቹን ኮንትራት ለማደስ ሙከራ ቢያደርግም እስካሁን ድረስ ስምምነት ላይ ባለመድረሳቸው ኦዚል ከቡድኑ ጋር የመለያየት እድሉ እየሰፋ መጥቷል።

በተለይ የዘንድሮ የፕሪምየር ሊግ ውድድር ከተጀመረ ጀምሮ እንደ ከዚህ ቀደም ለቡድኑ የጎላ ሚና መጫወት ባለመቻሉ ከደጋፊዎችም ትችት እየቀረበበት ይገኛል።

ባሳለፍነው ቅዳሜ መድፈኞቹ ወደ ቪካሬጅ ሮድ አቅንተው የማታ ማታ በዋትፎርድ ሲሸነፉ ጠንካራ ትችት የቀረበበት ይኸው ጀርመናዊ ሜሱት ኦዚል ነበር።

በእለቱ ባለሜዳዎቹ የአቻነቷን ጎል ከማስቆጠራቸው ቀደም ብሎ ኦዚል አርሰናሎች ጨዋታውን ሊገድሉበት የሚችሉበትን ግልጽ የጎል አጋጣሚ መጠቀም ሳይችል ቀርቷል።

አጋጣሚውን ወደ ጎል ለመቀየር የሞከረበት መንገድ ደካማ በመሆኑ እንዲሁም ግብጠባቂው በቀላሉ ኳሱን መቆጣጠር በመቻሉ ደጋፊዎች ለሽንፈቱ ምክንያት አድርገውታል።

ተጫዋቹ በቀጣይ ከቡድኑ ጋር ስለመቆየቱ የታወቀ ነገር ባይኖርም ኮንትራቱን አለመፈረሙን ተከትሎ ሌሎች የአውሮፓ ክለቦች እየተከታተሉት ይገኘሉ።

ከነዚህ ውስጥ ደግሞ ማንችስተር ዩናይትድ ይገኝበታል።ኦዚል ከጆሴ ሞሪንሆ ጋር በማድሪድ መስራቱ ደግሞ ዝውውሩ እውን ሊሆን የሚችልበት ሌላኛው ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ይጠበቃል።

ሚረር ጋዜጣም በዛሬ [አርብ] እትሙ ይህን የሚያጠናክር መረጃ ይዞ ወጥቷል።ጋዜጣው በጀርባ እትሙ ላይ ተጫዋቹ ለማንችስተር ዩናይትድ እንደሚፈርም የሚገልጽ ሲሆን ይህንንም ከወዲሁ ለቡድን ጓደኞቹ እንደነገራቸው ይጠቅሳል።

አርሰናሎች በተመሳሳይ የአሌክሲስ ሳንቼዝን ኮንትራት ያላራዘሙ በመሆኑ እንደ ኦዚል ሁሉ ተጫዋቹ ክለቡን የመልቀቅ እድሉ እየሰፋ መጥቷል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s