ማርኮ ቬራቲ የባርሴሎናን የዝውውር ጥያቄ ያልተቀበለበትን ምክኒያት አሳወቀ

ጣሊያናዊው ማርኮ ቬራቲ በክረምቱ የዝውውር መስኮት የባርሴሎናን ጥያቄ ችላ ብሎ በፒ ኤስ ጂ የቆየበት ምክንየት ተናግሯል።

የፒ ኤስ ጂ ጥበበኛ የመሀል ሜዳ ተጫዋች የሆነው ማርኮ ቬራቲን ለማዘዋወር የአውሮፓ ታላላቅ ቡድኖች ፍላጎታቸውን ሲያሳዩ ቆይተዋል።

በተለይ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ባርሴሎና ተጫዋቹን በጥብቅ ፈላጊ ሆኖ የቀረበ ቢሆንም ዝውውር ተፈጻሚ ሳይሆን ቬራቲ ከፓሪሱ ቡድን ጋር መቆየት ችሏል።

ቬራቲ ሌኪፕ ጋር ባነበረው ቆይታ በዝውውር መስኮቱ ወደ ባርሴሎና ያልሄደበት ምክንያት አሳውቋል።

“ሰዎች ለፒ ኤስ ጂ የምጫወተው ለገንዘብ እንደሆነ ያስባሉ።ነገርግን እዚህ የሚከፈለኝ ሌላ ቦታም አገኘዋለው

“በክረምቱ ወደ ሌላ ቡድን ለማምራት ብፈልግ ኖሮ 100 ሚሊየን ለዝውውሩ ለመክፈል እንዲሁም ለኔም ብዙ ደሞዝ የሚከፍለኝ ነበር

“ኔይማር ወደ ሲቲ ወይም ቼልሲ ቢያቀና ኖሮ እንደዚሁ ብዙ ይከፈለው ነበር።ነገርግን ለኛ የፈረመው በቡድኑ ፕሮጀክት ተማርኮ እንጂ ለገንዘብ አልነበረም።እኔም ልክ እንደሱ በማሰብ ነው የቆየሁት

ቬራቲ በዚህ ዙሪያ በክረምቱ ቀደም ብሎ ከክለቡ ጋር ንግግር አድርጎ በክለቡ ፕሮጀክት መደሰቱን ጨምሮ አሳውቋል።

Advertisements
Posted in Uncategorized

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s